ሚያዝያ ፮
(ከሚያዝያ 6 የተዛወረ)
ሚያዝያ ፮፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፲፮ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፲፩ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፶ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፵፱ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፰፻፷ ዓ/ም - የፋሲካ ማግሥት ዕለት መቅደላ አምባ ላይ የዓፄ ቴዎድሮስ ሠራዊት እና በሎርድ ኔፒዬር የተመራው የእንግሊዝ ሠራዊት ጦርነት ገጥመው፣ ድሉ የእንግሊዞች ሆነ። ንጉሠ ነገሥቱ ዓፄ ቴዎድሮስ በእንግሊዞች እጅ ከመውደቅ እራሳቸውን ማጥፋትን መርጠው ሽጉጣቸውን ጠጥተው ሞቱ። ቀብራቸው በመቅደላ መድኀኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ተከናወነ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አብዮት ከተጀመረ በኋላ ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴየልጅ ልጃቸው ልዑል ዘርዓ ያዕቆብ ተጠባባቂ/ምክትል አልጋ ወራሽ እንደሆኑ በይፋ አስታወቁ።
ልደት
ለማስተካከልዕለተ ሞት
ለማስተካከል- ፲፰፻፷ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ዓፄ ቴዎድሮስ ከእንግሊዝ ሠራዊት ጋር መቅደላ አምባ ላይ ጦርነት ገጥመው ሲሸነፉ በጠላት እጅ ከመውደቅ በገዛ ሽጉጣቸው እራሳቸውን ገደሉ።ቀብራቸውም በመቅደላ መድኀኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ተከናወነ።
ዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- (እንግሊዝኛ) http://www.nytimes.com/2011/04/16/opinion/16iht-oldapril16.html?_r=1&scp=4&sq=abyssinia&st=nyt
- (እንግሊዝኛ) http://www.thepeoplehistory.com/april14th.html Archived ኦገስት 13, 2011 at the Wayback Machine
- መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፣ ዕለታዊ የታሪክ ድርጊት - የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ (፲፱፻፶፩ ዓ/ም)
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1829 ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |