ጀርመናዊ ቋንቋዎች
(ከጀርማኒክ የተዛወረ)
ጀርመናዊ ቋንቋዎች የሕንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ ቅርንጫፍ ሲሆን፣ ሁላቸው ከቅድመ-ጀርማንኛ ደረሱ።
የጀርመናዊ ቋንቋዎች ፫ ክፍሎች ምዕራብ ጀርመናዊ፣ ስሜን ጀርመናዊ፣ እና ምሥራቅ ጀርመናዊ ሲሆኑ ከነዚህ አንዱ ምሥራቅ ጀርመናዊ አሁን ጠፍቶ አይገኝም።
ምዕራብ ጀርመናዊ ቋንቋዎች
ለማስተካከልዋና ቋንቋዎቹ እንግሊዝኛ፣ ሆላንድኛ፣ እና ጀርመንኛ ሲሆኑ፣ በነዚህ ውስጥ አያሌ ንዑስ ቀበሌኞች አሉ። ምዕራብ ጀርመናዊ ቋንቋዎች ይዩ።
ስሜን ጀርመናዊ ቋንቋዎች
ለማስተካከልእነዚህ ሁላቸው ከጥንታዊ ኖርስኛ ደረሱ። አሁን ዋናዎቹ ኖርዌይኛ፣ ስዊድኛ፣ ዳንኛ፣ አይስላንድኛ፣ ፋሮኛ ናቸው።
ምሥራቅ ጀርመናዊ ቋንቋዎች
ለማስተካከልእነዚህ ቋንቋዎች አሁን አይገኙም። ጎትኛ፣ የክሪሜያ ጎትኛ፣ ቫንዳልኛ፣ እና ቡርጉንድኛ ምሥራቅ ጀርመናዊ ልሳናት ነበሩ።