ጥቅምት ፲፱
(ከጥቅምት 19 የተዛወረ)
ጥቅምት ፲፱ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፵፱ኛው እና የመፀው ፳፬ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፫፻፲፯ ቀናት ሲቀሩ፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፲፮ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፰፻፶፮ ዓ.ም. - ጀኔቭ ላይ የተሰበሰቡ የአሥራ ስድስት አገሮች ልዑካን የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ማኅበር ለመመሥረት ተስማሙ። የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በ፲፱፻፳፰ ዓ.ም ተመሥርቶ በ፲፱፻፵፫ ዓ.ም. የዓለም አቀፋዊው ማኅበር አባል ሆነ። [1]
- ፲፱፲፭ ዓ.ም. - የኢጣልያው ንጉሥ ቪክቶር ኢማኑኤል ሦሥተኛ ለፋሽሽት መሪው ለቤኒቶ ሙሶሊኒ የጠቅላይ ሚኒስቴርነት ሥልጣን ሰጡ።
- ፲፱፻፲፮ ዓ.ም - በአንደኛው የዓለም ጦርነት የተሸነፈውና የተሠባበረው የኦቶማን ግዛት አክትሞ በቦታው የቱርክ ሪፑብሊክ ተመሠረተ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - የሱዳን መሪ ጄኔራል ሞሐመድ አቡድ በኢትዮጵያ የአንድ ሳምንት ጉብኝታቸውን ጀመሩ። በዚህ ጉብኝትም በንጉሠ ነገሥቱ ፴ኛ የዘውድ በዐል አከባበር ተሳትፈዋል።
- ፲፱፻፶፯ ዓ.ም. - በምሥራቅ አፍሪቃ ታንጋኒካ እና የዛንዚባር ደሴት ተዋሕደው የታንዛኒያ ሕብረት ሪፑብሊክን መሠረቱ።
ልደታት
ለማስተካከልዕለተ ሞት
ለማስተካከልዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- ^ http://www.redcrosseth.org/ http://www.icrc.org/IHL.nsf/FULL/115?OpenDocument Archived ጁላይ 31, 2012 at the Wayback Machine
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FO 371/154836 - Annual Report from Ethiopia for 1960
- {{en]] P.R.O., FCO 371/1829 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |