ጥቅምት ፲፫ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፵፫ኛው እና የመፀው ፲፰ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፪፻፳፫ ቀናት ሲቀሩ፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፳፪ ቀናት ይቀራሉ።

ሁንጋሪያ በ፲፱፻፵፱ ዓ.ም ተነስቶ የነበረውን ጸረ ስታሊን ሽብር እና አዲሲቱ የሁንጋሪያ ሪፑብሊክ በ ፲፱፻፹፪ ዓ.ም በአገሪቱ ፕሬዚደንት ማትያስ ስዙሮስ የታወጀበት ዕለት ማስታወሻ የብሔራዊ ቀን ነው።

  • ፲፱፻፬ ዓ/ም - በቱርክና በኢጣሊያ መካከል በነበረው ጦርነት የቱርኮችን የጦር ግንባር ከአየር ለመሰለል የኢጣልያ አውሮፕላንሊቢያ ተነሳ። ይሄም ድርጊት አውሮፕላን በጦርነት ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለበት ዕለት ነው።
  • ፲፱፻፴፫ ዓ/ም - ፔሌ በሚል ቅጽል ስሙ የሚታወቀው የብራዚል እግር ኳስ ተጫውች ኤዲሶን አራንቴስ ዶ ናሲሜንቶ ተወለደ። ፔሌ በዓለም የኦሊምፒክ ሸምቡድ[1] (International Olympic Committee) “የ፳ኛው ክፍለ ዘመን አትሌት” ብሎታል።

ዕለተ ሞት

ለማስተካከል

ዋቢ ምንጮች

ለማስተካከል
  1. ^ መስፍን አረጋ (ዲባቶ)፣ "ሰገላዊ አማርኛ፤ ፳፻ ዓ.ም
  • መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፤ ዕለታዊ የታሪክ ድርጊት - የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ (፲፱፻፶፩ ዓ/ም)
  • (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 31/165300 Ethiopia: Annual Review of 1961
  • (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1660 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1973የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ