ግንቦት ፳፰
(ከግንቦት 28 የተዛወረ)
ግንቦት ፳፰ ቀን፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፷፰ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፷፫ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፺፰ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፺፯ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፱፻፶፱ ዓ/ም - የእስራኤል አየር ኃይል የግብጽን፤ የዮርዳኖስን እና የሶርያን አየር ኃይል በቦምብ ሲደበድብ “የመካከለኛው ምሥራቅ የስድስት ቀን ጦርነት” ተቀጣጠለ። በዚህ ጥቃት ግብጽ አራት መቶ ያህል የጦር አየር ዠበቦች ሲወድሙባት፤ የዮርዳኖስ እና የሶርያ አየር ኃይሎች ከሞላ ጎደል ተደምስሰዋል።
- ፲፱፻፷ ዓ/ም - በአሜሪካ የፕሬዚደንት ምርጫ የዴሞክራት ቡድን እጩ የነበሩት ሮበርት ፍራንሲስ ኬኔዲ በነፍሰ ገዳይ ጥይት ሎስ አንጀለስ ከተማ ላይ ተመተው ነፍሳቸውን ለማዳን የሕክምና እርዳታ ሲቀበሉ አደሩ። ዳሩ ግን በማግሥቱ ግንቦት ፳፱ ቀን ሕይወታቸው አልፋለች።
ልደት
ለማስተካከልዕለተ ሞት
ለማስተካከል
ዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል
- (እንግሊዝኛ) http://en.wikipedia.org/wiki/June_5
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |