የእስፓንያ ነገሥታት ዝርዝር

አፈ ታሪካዊ ዘመን

ለማስተካከል

...

  • ተስታ - የሊብያ ኗሪ፣ 74 ዓመት (1426-1352 ግ. ዓክልበ.)
  • ሮሙስ - የተስታ ልጅ፣ 33 ዓመት (1352-1319 ዓክልበ.)
  • ፓላትዎስ - የሮሙስ ልጅ፤ 18 ዓመት (1319-1301 ዓክልበ.)
  • ካኩስ ሊኪንዩስ - መንግሥቱን ያዘ፣ 36 ዓመት (1301-1265 ዓክልበ.)
  • ፓላትዎስ - ወደ ዙፋን ተመለሰ፤ 6 አመት (1265-1259 ዓክልበ.)
  • ኤርትሩስ - የቲሮስ (ፊንቄ) ንጉሥ፣ 66 ዓመት (1259-1193 ዓክልበ.)
  • ጋርጋሪስ - የኤርትሩስ ልጅ፤ 75 ዓመት (1193-1118 ዓክልበ.)
  • ሄቢዴስ - የጋርጋሪስ ልጅ ልጅ፤ 49 ዓመት (1118-1069 ዓክልበ.)
  • ልድያ ሰዎች በእስፓንያ 48 ዓመት ገዙ (1069-1020 ዓክልበ.)
  • ጥራክያ ሰዎች 86 ዓመት ገዙ (1020-934 ዓክልበ.)
  • ሮዶስ ሰዎች 20 ዓመት ገዙ (934-914 ዓክልበ.)
  • ፍርግያ ሰዎች 26 ዓመት ገዙ (914-888 ዓክልበ.)
  • ቆጵሮስ ሰዎች 39 ዓመት ገዙ (888-849 ዓክልበ.)
  • የፊንቄ ሰዎች 41 ዓመት ገዙ (849-808 ዓክልበ.)
  • ግብጽ ሰዎች 35 ዓመት ገዙ (808-773 ዓክልበ.)
  • ሚሌሲያን ነገድ 29 ዓመት ገዙ (773-744 ዓክልበ.)
  • ካርያ ሰዎች 48 ዓመት ገዙ (744-696 ዓክልበ.)
  • ለስቦስ ሰዎች 68 ዓመት ገዙ (696-648 ዓክልበ.)
  • ፎኪያ ሰዎች 48 ዓመት ገዙ (648-600 ዓክልበ.)
  • ባቢሎን ንጉሥ 2 ናቡከደነጾር ከዚያ ለ9 (ወይንም ለ3) አመታት በእስፓንያ እንደ ነገሠ ይባላል። (ይህ ታሪካዊ ንጉሥ ቢሆንም፣ በእስፓንያ ግን እንደ ገዛ ማስረጃ ባለመኖሩ እንደ አፈ ታሪክ እንጂ በታሪክ ሊቃውንት የሚቀበል አይደለም።) (600-591 ዓክልበ.)

የቀርታግና አገረ ገዢዎች

ለማስተካከል

ከዚህ በኋላ የቀርታግና ሰዎች እስፓንያ ወረሩና ገዙ። የቀርታግና ሰዎች ቢያንስ በባሕር አጠገብ በእስፓንያ ከፊል በዕውነት እንደ ገዙ በታሪክ ሊቃውንት ይቀበላል።

የሮማ አገረ ገዦች

ለማስተካከል