ዩቤልዳ ወይም ዩባላኢዱቤዳጁባልዳእስፓንያ አፈ ታሪክ ዘንድ ከአባቱ ኢቤሩስ በኋላ (ምናልባት 2228-2162 ዓክልበ.) የእስፓንያ 3ኛው ንጉሥ ነበረ። ሰላማዊና ሃይማኖታዊ ንጉስ እንደ ነበር ይባላል።

የሰፈረበት አሁን በስሜን ስፔን ላ ሪዮሓ በተባለ ክፍላገር መሆኑ ይታመናል። በደቡብም ጂብራልታር ስሙን ከዚሁ ንጉሥ ስም አንዳገኘው ተብሏል፣ እንዲሁም በመካከለኛ እስፓንያ «ኢዱቤዳ» የተባሉ ተራሮች ለዚሁ ንጉሥ እንደ ተሰየሙ የሚሉ ደራስያን አሉ።

ቀዳሚው
ኢቤሩስ
ኢቤሪያ ንጉሥ ተከታይ
ብሪጉስ