ታጉስ ኦርማ
(ከታጉስ የተዛወረ)
ታጉስ ኦርማ በእስፓንያ አፈ ታሪክ ዘንድ ከብሪጉስ ቀጥሎ የኢቤሪያ 5ኛው ንጉሥ ነበረ። 30 ወይም 29 ዓመታት እንደ ነገሠ ይባላል (ምናልባት 2109-2081 ዓክልበ. ግድም)። በእርሱ ዘመን አገሩ ከርሱ ስም «ታጋ» እንደ ተባለ ይጻፋል። ከዚህ በላይ በእስፓንያና በፖርቱጋል የሚፈስሰው ታጉስ ወንዝ ስለእርሱ እንደ ተሰየመ የሚሉ መጻሕፍት አሉ። እንዲሁም ዛሬ ካርታሔና የምትባል ከተማ በመጀመርያው የታጉስ ከተማ ነበር የሚሉ አሉ።
በብዙ ምንጮች የብሪጉስ ልጅ ሲባል፥ በሌላው ደግሞ መታወቂያው ከጋሜር ልጅ ቴጋራማ ጋር አንድላይ እንደ ነበር ይታሥባል። ተከታዩ ልጁ ቤቱስ ይባላል።
ቀዳሚው ብሪጉስ |
የታጋ (ኢቤሪያ) ንጉሥ | ተከታይ ቤቱስ |