ሒሚልኮንቀርጣግና መርከበኛና ተጓዥ ነበረ። የግሪክ ጸሐፊ ትልቁ ፕሊኒ (1ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም.) እንደሚለን፣ ንጉሥ 2 ሓኖአፍሪካን ጠረፍ በተጓዘበት ዘመን (በ478 ዓክልበ. ግድም) ሒሚልኮን ደግሞ ከጋዲር ወጥቶ ወደ ስሜን በመዞር የአውሮጳን ጠረፍ ለመጓዝ ተላከ። ሆኖም ከፕሊኒና ከአዌኑስ (350 ዓ.ም. ግድም) ጥቅሶች በቀር፣ ስለ ሒሚልኮን ጉዞ ምንም መረጃ አሁን አይኖርም።

አዌኑስ እንደ ጠቀሰው፣ ከ4 ወር አደገኛ የመርከብ ጉዞ በኋላ «ዌስትሩምኒዴስ» ደሴቶች ደረሰ። ብዙ ቆርቆሮእርሳስ በዚያ በመገኘቱ፣ ከፊንቄያውያን አስቀድሞ የታርቴሶስ (ደቡብ እስፓንያ) ሰዎች ለንግድ ወደዚያ ይሔዱ ነበር። የደሴቶቹ ሥፍራ በትክክል ባይታወቅም በኮርንዋል (ደቡብ-ምዕራብ እንግሊዝ) ወይም በብረታኝ (ምዕራብ ፈረንሳይ) እንደ ተገኙ ይታሥባል። የቀርታግና ሰዎች (ፊንቄያውያን) የንግዳቸውን ምስጢር ለመጠብቅ የሌሎችን አገራት መርከበኞች ከምዕራብ ሜድትራኔያን ባሕር ውጭ እንዳይወጡ ይከለክሉ ነበር። በሒሚልኮን ታሪክ ዘንድ በጣም አደገኛና አስፈሪ ፍጡሮች የበዙበት መንገድ መሆኑን ሲለን፣ ይህ ምናልባት ግሪኮችና ሌሎች ተወዳዳሪዎች ለራሳቸው እንዳይጓዙበት ለማስፈራራት ይሆናል።

የውጭ መያያዣዎች ለማስተካከል