ሂስፓል ወይም ሂስፓሉስእስፓንያ አፈ ታሪክ ዘንድ ሄርኩሌስ ሊቢኩስ ሦስቱን ሎምኒኒ ከገደላቸው በኋላ በኢቤሪያ ዙፋን ላይ ያኖረው ንጉሥ ነበር። በልዩ ልዩ ታሪኮች ውስጥ የሄርኩሌስ ልጅ፣ ወንድም ልጅ፣ ወይም አለቃ ይባላል። በ600 ዓ.ም. ግድም የጻፈው ኢሲዶሬ ዘሰቪል እንደ ጻፈው ይሄ ሂስፓሉስ የእስፓንያ ሞክሼ ሲለው፣ ሌሎች ምንጮች ግን ስሙ ከሂስፓል ልጅ ሂስፓኑስ መሆኑን ያጠቁማሉ። «ሂስፓሊስ» የሚባለው ከተማ (የአሁን ሰቪያ) ለእርሱ እንደ ተሰየመ ደግሞ ይባላል።

ቀዳሚው
ሎምኒኒ
የኢቤሪያ ንጉሥ
2002-1970 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሂስፓኑስ