ኦሬክ (ሱመርኛ /ኡሩኡኑግ/አካድኛ: /ኡሩክ/፣ ግሪክ: Ορχόη /ኦርቆዔ/ ወይም Ωρύγεια /ኦሩገያ/አረብኛوركاء /ዋርካ/) የሱመር ጥንታዊ ከተማ በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ ነበረ። በአለሙ ላይ ከሁሉ ጥንታዊ ትልቅ ከተሞች አንዱ ነው።

በኦሬክ የተገኘ ጥንታዊ የበሬ ቅርጽ

ጥንታዊ ሠፈሩ ደግሞ ኩላብ ወይም ኡኑግ-ኩላባ ይባል ነበር። በሱመር ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ እንዲሁም በአፈ-ታሪክ «ኤንመርካርና የአራታ ንጉሥ» ዘንድ የመሠረተው ንጉስ ኤንመርካር ነበር። እንዲሁም በመጽሐፈ ቅዱስ ምስክር ዘንድ በሰናዖር የመሠረተው ናምሩድ ነበር (ዘፍጥረት 10፡10)። በኋላ ዘመንም የጊልጋመሽ ከተማ ነበረ።

የኡሩክ ነገሥታት

ለማስተካከል

ከዚህ በኋላ፣ ላጋሽ፣ አዳብማሪአክሻክ፣ ኪሽ፣ ኡርና ኡማ ላዕላይነቱን ለመያዝ ይወዳደሩ ነበር።