ኤንሻኩሻናሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ላይ የኡሩክ ንጉሥ ሲሆን ከሐማዚ ንጉሥ ሀዳኒሽ በኋላ በሱመር ላዕላይነቱን ለ60 አመታት ያዘ። በዚህ ዝርዝር ያሉት ቁጥሮች ግን ታማኝ አይደሉም፤ ብዙ ጊዜም በእጥፍ ተረዠሙ። ዘመኑ ምናልባት 2215-2195 ዓክልበ. ግድም እንደ ነበር ይመስላል። ኤንሻኩሻና ሐማዚንና የኪሽን ንጉሥ ኤንቢ-ኢሽታርን አሸነፈ፤ ከዚህ በላይ በኒፑርአካድአክሻክ ከተሞች ላይ ሥልጣን ያዘ። ልጁ ሉጋል-ኪኒሼ-ዱዱ በኡሩክ የተከተለው ሲሆን፣ ዋና ተወዳዳሪያቸው የላጋሽ ንጉሥ ኤአናቱም ግን ዑርን በመያዝ በላዕላይነት እንዳሸነፈ ይመስላል።

በአንድ ሰነድ ዘንድ የኪሽን ንጉሥ ኤንቢ-እሽታርን ማርኮ ኪሽን አጠፋ፣ የኪሽንና የአክሻክንም ሰዎች እንዳዛወረ ይላል።[1]

ቀዳሚው
ሐማዚ ንጉሥ ሀዳኒሽ
ሱመር አለቃ
2215-2195 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ላጋሽ ንጉሥ ኤአናቱም
ቀዳሚው
ሉጋል-ኪቱን ?
ኡሩክ ንጉሥ
2215-2195 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሉጋል-ኪኒሼ-ዱዱ
  1. ^ ጥንታዊ ሰነዶች Archived ኦገስት 23, 2011 at the Wayback Machine - ጣልኛ