ግሪክ (ቋንቋ)
የግሪክ ቋንቋ ወይም ግሪክኛ (Ελληνικά /ኤሊኒካ/) ከህንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች አንዱ ሲሆን የግሪክ (የአገሩ) እንዲሁም የቆጵሮስ መደበኛ ቋንቋ ነው። በጠቅላላ ከ15 ሚሊዮን ሰዎች በላይ ይናገሩበታል። ቀደም ሲል ደግሞ በሜዲቴራኔያን ዙሪያ፣ በምዕራብ እስያና በስሜን አፍሪቃ በሰፊ ይጠቀም ነበር።
ግሪክ የተጻፈበት በግሪክ አልፋቤት ነው። ዛሬ በዓለም ዙርያ አብዛኞቹ ፊደሎች በተለይም የላቲን አልፋቤትና የቂርሎስ አልፋቤት የተለሙ ከዚሁ ግሪክ ጽሕፈት ነበር። ግሪኮቹ ደግሞ ሀሣቡን የበደሩ ከፊንቄ አልፋቤት ምናልባት በ1100 ዓክልበ. ገዳማ ነበረ። ከዚያ በፊት (1500-1100 ዓክልበ. ግድም) ከሥነ ቅርስ እንደ ታወቀ ግሪክኛ በፍጹም በሌላ ጽሕፈት «የሚውኬናይ ጽሕፈት» ይጻፍ ነበር።