ማሪመስጴጦምያ ጥንታዊ ከተማ ነበር። ዛሬው ሥፍራው በአረብኛ ተል ሐሪሪ ተብሎ ብዙ ጽላቶች የተገኙበት ፍርስራሹ በዘመናዊው አገር ሶርያ ውስጥ በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ ይገኛል።

ማሪ
(ተል-ሐሪሪ)
የማሪ ፍርስራሽ
ሥፍራ
ማሪ is located in Syria
{{{alt}}}
ዘመን 2350-1673 ዓክልበ.
ዘመናዊ አገር ሶርያ
ጥንታዊ አገር ማርቱ

የማሪ ነገሥታት

ለማስተካከል

ከማሪ ጽላቶች እንዲሁም ከኤብላ ጽላቶች ከተገኘው በርካታ መረጃ የማሪ ነገሥታት ዘመኖች ሊታወቅ ይቻላል።

መጀመርያ የሚታወቀው የማሪ ንጉሥ በኡር ንጉሥ መስ-አኔ-ፓዳ ዘመን (2345-2314 ዓክልበ. ግ.) የነገሠው ጋንሱድ ይመስላል። ጋንሱድ ከመስ-አኔ-ፓዳ ጋር በዚህ ዘመን ንግድ እንዳካሄደው ይታወቃል። ከዚያ በኋላ የላጋሽ ንጉሥ ኤአናቱም ግዛቱን እስከ ማሪ ድረስ አስፋፋ። በኤአናቱም መሞት (2195 ዓክልበ. ግ.) ማሪ እንደገና ነጻ መንግሥት ሆነ።

አካድ ንጉሥ ታላቁ ሳርጎን ማሪን ያጠፋው በኢሽቂ-ማሪ ፱ኛው ዓመት ይመስላል። ከዚያ በአካድ መንግሥት ዘመን አለቃው ኢዲዲሽ በማሪ ላይ ተሾመ። ከእርሱ በታች «ሻካናኩ» (ሻለቆቹ) የተባለው ኟሪ ወገን በማሪ ተነሣ። እነርሱም፦

...

በ1673 ዓክልበ. ማሪ ለባቢሎን ንጉሥ ሃሙራቢ ወደቀ።