ቡሩሻንዳ ወይም ፑሩሽሐቱም የጥንታዊ ሐቲ (አሁን በቱርክ) ከተማ ነበር። ሥፍራው ዛሬ ለሥነ ቅርስ እርግጥኛ አይደለም። ከቱዝ ጎሉ ሐይቅ ደቡብ እንደ ተገኘ ይታስባል።

ፑሩሽሐቱም

ኬጥኛ የተጻፈው ግጥም የውግያ ንጉሥ ስለ ታላቁ ሳርጎን ምዕራብ ዘመቻ ነው። ይህ ጽሑፍ በአካድኛ ትርጉም ደግሞ በአሦርና በአማርና ደብዳቤዎች መካከል (በግብጽ) ተገኝቷል። ሳርጎን በጥልቅ በሐቲ አገር እንደ ዘመተ ይናገራሉ። ጽሁፉ እንደሚተርከው፣ በሐቲ በካነሽ የኖሩት አካዳዊ ነጋዴዎች በቡሩሻንዳ ንጉሥ ኑርዳጋል ስለ ተበደሉ ሳርጎን በሩቅ መንገድ ከሠራዊቱ ጋር መጥቶ ኑርዳጋልን እንዲቀጣው በሚል ልመና ልከው አስረዱት። የኑርዳጋል ሰዎች በጸጥታቸው እየኮሩ ዝም ብሎ የሳርጎን ሥራዊት ደረሰና ቶሎ አሸነፋቸው። ሦስት ዓመት በቡሩሻንዳ ቆይተው የከተማውን ግድግዶች ሰበሩ ይላል። ይህ ታሪክ ግን ከገለጸው ዘመን በኋላ እንደ ተጻፈ ይታስባል።

ከዚህ በኋላ በካነሽ ንጉሥ አኒታ ዘመን ሰነዶች ውስጥ ቡሩሻንዳ እንደገና ይጠቀሳል። የቡሩሻንዳ ንጉሥ ለአኒታ እጅ እንደ ሰጠ ይላል። ይህ የካነሽ ግዛት በኋላ የኬጥያውያን መንግሥት ሆነ።