ገብስ
ገብስ (ሮማይስጥ፦ Hordeum vulgare) የእህል አይነት ነው። እንዲሁም እህሉ ከዘሮቹ የመጣው የሣር ተክል አይነት ነው። ከጥንት ጀምሮ ለሰዎች ምግብና ለእንስሶች መኖ ይጠቅማል፤ ከዚህም በላይ ብቅል በማድረግ ቢራና ሌላ መጠጥ ለመሥራት ይጠቀማል። ከእህሉም የወጣው ዱቄት እንደ ዳቦ ሊሠራ ይችላል። ይህ እህል ለዕድሜ እጅግ ጤነኛ ምግብ መሆኑ ይታወቃል።
የገብስ ዱቄት በውሃ ለሆድ ቁስል (አልሰር) ይበላል።[1]
- ^ የፍቼ፣ ኦሮሚያ ባህላዊ መድሃኒት ጥናት 2006 ዓም ከዓቢዩ እኒየው እና ሌሎች፣ ጎንደርና አዲስ አበባ ኡኒቨርሲቲዎች ሥነ ፍጥረት ኮሌጆች