የፈተና ደንጊያ
የፈተና ደንጊያ የወርቅ ወይም ሌላ ውድ ብረታረት ጥረት የሚፈትን ድንጋይ መሣሪያ ነው።
ወርቅ በድንጋዩ ላይ ሲፈተግ፣ በሚያስቀምጠው ምልክት ቀለም ወርቁ ጥሩ እንደ ሆነ ወይም የተደባለቀ እንደ ሆነ ማወቅ ይቻላል።
ይህ ዘዴ ለሕንድ ሸለቆ ሥልጣኔ (ምናልባት 2400-1900 ዓክልበ. ያሕል) እንደ ታወቀ ከሥነ ቅርስ ታውቋል። ለረጅም ዘመን ግን ጥቅሙ ሰፊ አልሆነም። በግብጽ የፈተና ደንጊያ ከ1200 ዓክልበ. ግድም ጀምሮ ተገኝቷል። በፈረንሣይ በተገኘ ሥነ ቅርስ ሥፍራ ከ700 ዓክልበ. ግድም በዚያ እንደ ታወቀ ያስረዳል።
ከዚህ በላይ የዚሁ ፈጠራ ጥቅም በዚያ ዘመን ያህል ለልድያ ሰዎች ስለ ታወቀ፣ መጀመርያ መሐለቅ በተጠራ ብረታብረት እንደ ተሠራ በማረጋገጥ አዲስ የገንዘብ ገበያ በማስገባታቸው ንግድ ለዘለቄታ ቀየሩ። የግሪክ አገር ሰዎች በቋንቋቸው «የልድያ ደንጊያ» ሲሉት ዘዴውን ከዚያ እንደ ተማሩት ያሳምናል።
በሥነ ጽሑፍ የፈተና ደንጊያ መጀመርያ የሚጠቀስ በግሪኩ ጤዮግኒስ ዘመጋራ ቅኔ (550 ዓክልበ. ግድም) ሲሆን፣ በ፬ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. የሕንድ ጽሐፊ ካውጢልያ እና የግሪክ ጸሐፊ ጤዎፍራስቶስ ስለ ፈተና ደንጊያ ጥቅም በሰፊ ገለጹ። እንዲሁም ፕሊኒ (71 ዓ.ም.) ስለ ፈተና ደንጊያ ይገልጻል።
ዋቢ መጽሐፍ
ለማስተካከል- Shannon Venable፣ 2011, Gold: A Cultural Encyclopedia p. 264-5. (እንግሊዝኛ)