ኅዳር ፲፱ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፸፱ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፹፯ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፹፮ ቀናት ይቀራሉ።

ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች

ለማስተካከል

፲፭፻፲፫ ዓ.ም. በፈርዲናንድ ማጄላን መሪነት የተቀናጁ ሦሥት የፖርቱጋል መርከቦች በደቡብ አሜሪካ ደቡባዊ ጫፍ የባሕር መስመር አልፈው ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ወደ ሰላማዊ ውቅያኖስ በመሸጋገር የመጀመሪያዎቹ አውሮፓውያን ሆኑ።

፲፰፻፴፮ ዓ.ም. በሐዋይ ደሴቶች የነጻነት ዕለት ነው። የብሪታንያ እና የፈረንሳይ መንግሥታት የሐዋይን ደሴቶች ንጉዛት (ንጉሣዊ + ግዛት)ሉዐላዊነት አወቁ፣ አከበሩ።

  • ፲፰፻፵፭ ዓ/ም - የደጅ አዝማች ካሣ (በኋላ ዓፄ ቴዎድሮስ)ሠራዊትና የጎጃሙ የደጅ አዝማች ጎሹ ተከታዮች ጉራምባ ላይ ተዋግተው ድሉ የደጅ አዝማች ካሣ ሆነ። ደጅ አዝማች ጎሹም በነፍጥ ተመተው ሞቱ።

፲፱፻፭ ዓ.ም. አልባኒያኦቶማን ግዛትነት ነጻነቷን አወጀች።

፲፱፻፴፮ ዓ.ም. የአሜሪካው ፕሬዚደንት ፍራንክሊን ሩዝቬልት፣ የብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስቴር ዊንስተን ቸርቺል እና የሶቪዬት ሕብረት መሪ ጆሴፍ ስታሊን ኢራን ዋና ከተማ ቴህራን ላይ ተገናኝተው ከናዚ ጀርመን ጋር ለሚያካሂዱት ጦርነት የሕብረት ስልት አውጥተው፣ ተስማምተው ተለያዩ።

፲፱፻፶፩ ዓ.ም. ቅኝ ግዛቶች የነበሩት ቻድ፣ የኮንጎ ሪፑብሊክ እና ጋቦንፈረንሳይ ቤተሰብ ስር እራሳቸውን ማስተዳደር ጀመሩ።

፲፱፻፶፫ ዓ.ም. ሞሪታንያፈረንሳይ ቅኝ ግዛትነት ነጻነቷን ተቀዳጀች።

፲፱፻፷፰ ዓ.ም. የፖርቱጋል ቅኝ ግዛት የነበረችው ምሥራቅ ጢሞር፣ ገዥዋ ስትተዋት የራሷን ነጻነት አወጀች። ከዘጠኝ ቀናት በኋላ ግን በኢንዶኔዚያ ሠራዊቶች ተወራ የኢንዶኔዚያ ሃያ ሰባተኛ አውራጃ ሆነች።

፲፱፻፹፫ ዓ.ም. በብሪታንያ “ኮንሰርቫቲቭ” የቀኝ ፖለቲካዊ ቡድን መሪ የነበረችው ማርጋሬት ታቸር ከመሪነቷ ካስወገዷት በኋላ የጠቅላይ ሚኒስቴርነቱን ስልጣን ለአገሪቷ ንግሥት ዳግማዊት ኤልሳቤጥ አስረከበች። ከአሥራ አምሥት ደቂቃ በኋላ ንግሥቲቱ አዲሱን የ”ኮንሰርቫቲቭ” ቡድን መሪ ጆን ሜጀርን አቅርባ፣ አዲስ አስተዳደር በጠቅላይ ሚኒስቴርነት እንዲመራ ሾመችው።

ዕለተ ሞት

ለማስተካከል

ዋቢ ምንጮች

ለማስተካከል
  • (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1829 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974