ኅዳር ፳፱ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፹፱ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፸፯ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፸፮ ቀናት ይቀራሉ።

ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች

ለማስተካከል
  • ፲፱፻፷፭ ዓ/ም -የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ፯መቶ፰ ከአዲስ አበባ ተነስቶ አስመራአቴናሮማ እና ፓሪስ ለመሄድ ከነዠበብተኞቹ ዘጠና አራት ሰዎች ጭኖ በተነሳ በአሥራ ሦስት ደቂቃዎች ከመንገደኞቹ መኻል ፭ ወንዶችና ፪ ሴቶች ሽጉጥ መዝዘው በአማርኛ ትዕዛዛቸውን ሲጮኹ የአየር መንገዱ የጸጥታ ሰራተኞች ተኩስ ከፍተው ስድስቱን ጠላፊዎች ሲገድሉ ሰባተኛው በኋላ ሆስፒታል ገብቶ ሞቷል። በተኩሱ ጊዜ ከጠላፊዎቹ አንዱ የያዘውን የእጅ ቦምብ ነቅሎ ሲጥለው ከመንገደኞቹ አንዱ ብድግ አድርጎ ሰው ወደሌለበት ሥፍራ ጥሎት ፈነዳ። ይኽ ፍንዳታ አንድ ሞተር እና የአቅጣጫ መቆጣጠሪያውን ከጥቅም ውጭ ሲያደርገው የአየር ዠበቡን የመንገደኞች ክፍል በጢስ አፍኖት ነበር። ኣብራሪው አየር-ዠበቡን ወደ አዲስ አበባ መልሶ በሰላም አሳርፎታል። ጠላፊዎቹ [[የኤርትራ ነጻነት ግንባር] አባላት ነበሩ።

ዕለተ ሞት

ለማስተካከል

ዋቢ ምንጮች

ለማስተካከል