ኅዳር ፫
ኅዳር ፫ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፷፫ኛው እና የመፀው ወቅት ፴፰ተኛ ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፫፻፫ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፪ ቀናት ይቀራሉ።
ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች
ለማስተካከል- ፲፰፻፴፬ ዓ/ም - በእስክንድርያው ፓትርያርክ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስነት የተሾሙት አቡነ ሰላማ በዚህ ዕለት ደረስጌ ሲገቡ ደጃዝማች ውቤ በደማቅ ሥርዓት ተቀበሏቸው።
- ፲፱፻፳ ዓ.ም. - በሶቪዬት ሕብረት የሥልጣን ውድድር ሊዮን ትሮትስኪ በግዞት ከአገር ውጭ እንዲወጣ ሲደረግ የጠቅላይ መሪነት ሥልጣን ወደ ጆሴፍ ስታሊን ተላለፈ።
- ፲፱፻፴፩ ዓ.ም. - በአሥራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን በነበረ ቴዎድሮስ ኸርዝል በሚባል ጋዜጠኛ ለመጀመሪያ የተጠቆመውን ማለትም ማዳጋስካርን “የአይሁዶች አገር” ይደረግ የሚለውን ሐሣብ፤ በ ጀርመን የናዚው የፕሮፓጋንዳ ሚኒስቴር ኸርማን ገሪንግ ዕቅድ አቀረበ።
- ፲፱፻፸፭ ዓ.ም. - በፖሎኝ በገዢው የኮሙኒስት ፓርቲ “ህገ ወጥ” ተብሎ የታገደው የ “ሶሊዳሪቲ” ቡድን (Solidarity Party) መሪ የነበረው፣ በኋላ የአገሪቱ ፕሬዚደንት የሆነው ሌክ ቫሌሳ ከአሥራ አንድ ወራት እሥራት በኋላ ተፈታ።
- ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. - በጃፓን፣ አልጋ ወራሹ አኪሂቶ የአገሪቱ መቶ ሃያ አምስተኛው ንጉሠ ነገሥት ሆነው ንጉሠ ነገሥት አኪሂቶ በመባል በአባቶቻቸው ዙፋን ላይ ተቀመጡ።
ልደት
ለማስተካከልዕለተ ሞት
ለማስተካከል- ፲፱፻፺፩ ዓ.ም. - ኢትዮጵያዊው 'የቀለም ሰው' ክቡር ዶክቶር ከበደ ሚካኤል በተወለዱ በሰማንያ ሁለት ዓመታቸው አረፉ።
ዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፤ ዕለታዊ የታሪክ ድርጊት - የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ (፲፱፻፶፩ ዓ/ም)
- (እንግሊዝኛ) http://news.bbc.co.uk/onthisday/hi/dates/stories/november/12/newsid_3151000/3151758.stm
- (እንግሊዝኛ) http://www.nytimes.com/learning/general/onthisday/20081112.html
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |