መስከረም ፳፮
በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፳፮ኛው ዕለት እና የመፀው የመጀመሪያው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፫፻፵ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ዮሐንስ ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፴፱ ዕለታት ይቀራሉ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዕምነት ተከታዮች "ዘመነ ጽጌ" ወይም "ወርኅ ጽጌ" የሚባለውን የማርያምን ስደት መታሰቢያ የ ፵ ቀን የጽጌ ፆም በዛሬው ዕለት ጀምረው ኅዳር ፮ ቀን ይፈቱታል።
፲፰፻፹፪ ዓ/ም -ቶማስ ኤዲሶን የተባለው አሜሪካዊ የፈጠራ ሰው የመጀመሪያውን ተንቀሳቃሽ ምስል (motion picture) አሳየ።
፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የግብጽ ሠራዊት በእስራኤል ላይ የ’ረመዳን ጦርነት’ ወይም የ’ዮም ኪፑር’ ጦርነት በመባል የሚታወቀውን የስድስት ቀን ውጊያ ከፈቱ።
፲፱፻፸፬ ዓ/ም - የግብጽ አመጸኛ መኮንኖች ፕሬዚደንታቸውን አንዋር ሳዳትን አደባባይ ላይ በጥይት ደብድበው ገደሏቸው።
ልደት
ለማስተካከልዕለተ ሞት
ለማስተካከል፲፬፻፬ ዓ/ም - በ፲፫፻፸፭ ዓ/ም በኢትዮጵያ ዙፋን ላይ ተቀምጠው ለሃያ ዘጠኝ ዓመት የነገሡትና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ግማደ መስቀል ወደኢትዮጵያ ያስመጡት ዳግማዊ ዓፄ ዳዊት ፈረሳቸው ረግጧቸው ሞቱ። [1]
፲፱፻፸፬ ዓ/ም የኖቤል የሰላም ሽልማት ተቀባይ እና የግብጽ ሦስተኛው ፕሬዚደንት አንዋር ሳዳት በአመጸኛ መኮንኖች እጅ ተገደሉ።
ዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- ^ መሪ ራስ ኤ ኤም በላይ፣ «የጥንቷ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ታሪክ'» (፲፱፻፹፭ ዓ/ም)፣ ቦሌ ማተሚያ ድርጅት
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |