ሐምሌ ፲፪
ሐምሌ ፲፪ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፲፪ኛው ቀን ሲሆን የክረምት ወቅት ፲፯ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፶፬ ቀናት፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፶፫ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፯፻፸፩ ዓ/ም- የጎጃም መስፍን ደጅ አዝማች ክንፉ አዳም ንጉሥ ሰሎሞንን በነገሡ በዓመት ከአሥር ወር በኋላ ከዙፋናቸው አውርደው አሥረው አቤቶ ተክለ ጊዮርጊስን በቦታቸው አነገሡ።
- ፲፰፻፶፪ ዓ/ም - በሰሜን ሰላማዊ ውቅያኖስ ላይ የጀመረው ሙሉ የፀሐይ ግርዶሽ፣ ሰሜን አሜሪካን፤ አትላንቲክ ውቅያኖስን፣ አውሮፓን እና ሰሜን አፍሪቃን አቋርጦ ምጽዋ አካባቢ ሲደርስ በጀመረ በሦስት ሰዓት ገደማ አብቅቷል።[1]
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - ፕሮፌሶር መስፍን ወልደ ማርያም በኢትዮጵያ አብዮት የባለ ሥልጣናትን ሙስና እና የሥልጣን ወንጀል እንዲመረምር ለተመሠረተው ሸንጎ ሊቀ መንበር እና ምክትላቸው ደግሞ ሻለቃ መሸሻ አድማሱ እንደሆኑ ይፋ ተደረገ።
ልደት
ለማስተካከልዕለተ ሞት
ለማስተካከልዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፤ ዕለታዊ የታሪክ ድርጊት - የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ (፲፱፻፶፩ ዓ/ም)
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1829 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |