ጥር ፩
(ከጥር 1 የተዛወረ)
ጥር ፩ ቀን፦
በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፳፩ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፵፭ ቀናት፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፵፬ ቀናት ይቀራሉ።
ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች
ለማስተካከል- ፲፯፻፸፪ ዓ/ም - ታብሪዝ በምትባለዋ የፋርስ (አሁን ፐርሺያ) ከተማ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የ፹ሺ ሰዎችን ሕይወት አጥፍቷል።
- ፲፰፻፸ ዓ/ም - ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛትነት የተመኟት እና የአድዋ ጦርነት እንዲጀመር ያዘዙት የኢጣልያ ንጉሥ ቀዳማዊ ኡምቤርቶ በዛሬው ዕለት ዳግማዊ ቪቶሪዮ ኢማኑኤል ሲሞቱ ዙፋኑን ወረሱ።
- ፲፱፻ ዓ/ም - ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ እና በኢትዮጵያ የፈረንሳይ መንግሥት ዋና መላክተኛ ክሎቡኮውስኪ የንግድ እና ወዳጅነት ስምምነት አዲስ አበባ ላይ ተፈራረሙ።
- ፲፱፻፵፫ ዓ/ም ኒው ዮርክ ከተማ የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሕንጻ ተመረቀ።
- ፲፱፻፺፫ ዓ/ም ‘አፕል’ (Apple Computer Inc.) የተባለው የአሜሪካ የመቀምር ድርጅት ‘አይ ቲዩንስ’ (iTunes) የተባለውን የሙዚቃ ተሰኪ ስብስብ አካል (software) ሳን ፍራንሲስኮ ላይ አስተዋወቀ።
- ፲፱፻፺፱ ዓ/ም ‘አፕል’ (Apple Computer Inc.) “አይ ፎን” (iPhone) የተባለውን ተንቀሳቃሽ ስልክ አስተዋወቀ።
ልደት
ለማስተካከልዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |