የካቲት ፳፩
(ከየካቲት 21 የተዛወረ)
የካቲት ፳፩፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፸፩ ኛው ዕለት ሲሆን፤ የበጋ ወቅት ፶፮ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፺፭ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፺፬ ቀናት ይቀራሉ።
ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች
ለማስተካከል- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በጎ አድራጎት ድርጅት በአዋጅ ቁጥር ፪፻፷፩/፶፪ መሠረት ፀደቀ። የድርጅቱ ማቋቋሚያ የአደራ መስጫ ሰነድ (ቻርተር) በሐምሌ ፲፭ ቀን ፲፱፻፶፩ ዓ/ም በመንግሥት ማስታወቂያ ቁጥር ፪፻፶፫/፶፩ መሠረት ወጥቶአል። ይህ ድርጅት በጥቅምት ወር ፲፱፻፷፮ ዓ/ም የደርግ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት በአዋጅ እስከወረሰው ድረስ አገልግሏል።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - በሞሮኮ የተከሰተ የመሬት እንቅጥቅጥ አጋዲር የተባለችውን ከተማ አወደመ።
- ፳፻፭ ዓ/ም - የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ፖፕ ቤኔዲክት ፲፮ኛ «የዕድሜያቸው መግፋት የተደራረበ ሓላፊነታቸውን በአግባቡ ለመወጣት ስላላስቻላቸውና በሚታይባቸው አካላዊ ድካምና አቅም ማጣት» በሚል ምክንያት ሥልጣናቸውን ለቀቁ።
ልደት
ለማስተካከልዕለተ ሞት
ለማስተካከል- ፲፯፻፴፫ ዓ/ም - የሸዋው መስፍን መርድ አዝማች አብዬ አረፉ። ቀብራቸውም በሐር አምባ ሚካኤል ተከናወነ። ልጃቸው መርድ አዝማች አምኃ ኢየሱስ ተተክተው ምስፍናውን ያዙ።
ዋቢ ምንጮች
ለማስተካከልhttp://www.ethiopianreporter.com/index.php?option=com_content&view=article&id=1314:2010-02-24-08-32-54&catid=105:2009-11-13-13-47-17&Itemid=625 Archived ማርች 4, 2016 at the Wayback Machine
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |