የብርሃናት ክፍለ ዘመን
ዘመነ አብርሆት (ፈረንሳይኛ፦ le Siècle des Lumières /ለ ሲዬክል ዴ ሉምዬር/፣ ጀርመንኛ፦ Aufklärung /አውፍክላሩንግ/ «ማብራራት»፣ እንግሊዝኛ፦ Enlightenment /እንላይተንመንት/ «ማብራራት») በተለይ በ18ኛው ክፍለ ዘመን የተከሠተው፣ ከ17ኛው ክፍለ ዘመን «ሳይንሳዊ አብዮት» የተከተለ የዘመናዊ ፍልስፍና እንቅስቃሴ ነበረ። «የፍልስፍና ክፍለ ዘመን» ወይም «የምክንያት ዘመን» ተብሏል።
እንቅስቃሴው የተጀመረው በፈረንሳይ ሲሆን፣ በተለምዶ ከ1707 እስከ 1781 ዓም ድረስ እንደ ቆየ ይቆጥሩታል። ከፈረንሳይ የ«ማብራራት» ሀሣቦች በተለይ ወደ እስፓንያ፣ ጀርመን፣ ፖላንድ፣ ሩስያ፣ ግሪክ፣ ስኮትላንድና አሜሪካ ተስፋፉ። በሌሎች አገራት ግን ለምሳሌ በእንግላንድ ወይም በጣልያን፣ «ማብራራቱ» አነስተኛ ሚና አጫወተ።
በዚህ ወቅት ዘመናዊ ከነበሩት ሃሣቦች መሃል፦
እንዲሁም በዚህ ወቅት የምጣኔ ሀብት፣ የሕገ መንግሥት፣ የአርነት፣ የትምህርት ፍልስፍናዎች እየተደረጁ ነበር። መደበኛ የክርክር ማህበር ሥርዓትና ቡና ቤት (ቡና የሚጠጣበት ሰዎችም የሚወያዩበት) ዘመናዊ ሆኑ። እንዲሁም የንጉሥ ወይም የፓፓ ሥልጣናት ተጽእኖ ይቀነስና ሕዝባዊነት፣ ተጠራጣሪነት ይበዛ ነበር።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |