ምክኑያዊነት (rationalism) ዕውቀት የሚገኘው በመሪ ሐሳቦች እና በምክንያት ነው የሚል የሐሳባዊ ዓይነት ፍልስፍና ነው። በጥሩ አመክንዮ ሊደረስባቸው የማይችሉ ዕውቀቶችን፣ ለምሳሌ ሥሜታዊነትን፣ ሃይማኖታዊ ተዓምራትን፣ ከሕዋሳት የሚፈልቁ ግንዛቤዎችን፣ ባጠቃላይ መልኩ አይቀበልም።

አንድ አውሮፕላን፣ መሬት ላይ እያለ ግዙፍ ቢመስልም፣ አየር ላይ ሲዎጣ ጥንጥ ይመስላል። ነገር ግን ማንም እንደሚገነዘብ የአውሮፕላኑ ግዝፈት ምንጊዜም እኩል ነው። ይህን የአለመቀያየር ሁኔታ እምናውቀው በሚዋሸን የሥሜት ሕዋሳታችን (ዓይናችን) ሳይሆን በአዕምሮ ውስጥ ባለን የተፈጥሮ የአስተሳሰብ መርህ ነው ያላል ምክኑያዊነት።

ከዚህ የፍልስፍና ዓይነት ትይይዩ የሚቆመው ፍልስፍና፣ ዳሳሻዊነት ሲባል፣ ስለ ዓለም እምናውቀው ዓለምን በሕዋሶቻችን በመመርመር እንጅ ውስጣዊ መሪሃሳቦችን በምክንየት በማያያዝ አይደለም ያላል።