ኢሲን ከ1900 እስከ 1709 ዓክልበ. ድረስ የሱመር መጨረሻ ከተማ-ግዛት ነበረ።

በ1900 ዓክልበ. የኡር መንግሥት ሥልጣን እየደከመ የኢሲን ገዥ እሽቢ-ኤራ ከኡር ነጻነቱን አዋጀ። ከጥቂት አመት በኋላ በ1879 የኤላም ሕዝቦች ኡርን ዘረፉና የኡር መንግሥት ሲወድቅ ኢሲን ያንጊዜ ላዕላይነቱን በሱመር ያዘ። የኢሲን ንጉሶች እጅግ አረመኔ ተከታዮች ነበሩ።

በ1844 የላርሳ ከተማ ገዥ ጉንጉኑም በተራው ነጻነቱን ከኢሲን አዋጀና 2 ከተሞቹ ብርቱ ተፎካካሪዎች ሆኑ። ከ1835 ጀምሮ ጉንጉኑም ኡርን ያዘ። በ1832 የኢሲን ንጉሥ ሊፒት-እሽታር ሕገ መንግሥትን አወጣ።

በ1807 የባቢሎን ገዥ ሱሙ-አቡም ደግሞ በተራው ነጻነቱን አዋጀ። ኢሲን፣ ላርሳና ባቢሎን በተለይ ለላዕላይነቱ ተወዳዳሪዎች ሆኑ። ሦስቱ መንግሥታትና ጎረቤቶቻቸው - ካዛሉኪሡራኤሽኑናአሦርአሞራውያንኤላም ወዘተ. - ደግሞ ይወዳደሩ ነበር። በ1772 ኤንሊል-ባኒ የኢሲንን ዙፋን ያዘ። ከርሱ ዘመን በኋላ የኢሲን ሃይል ደከመ፤ በመጨረሻ የባቢሎን ንጉሥ ሲን-ሙባሊት በ1709 ዓክልበ. ኢሲንን ያዘው። በ1705 የላርሳ ንጉሥ ሪም-ሲን ያዘው። በ1699 የባቢሎን ንጉሥ ሃሙራቢ እንደገና ኢሲንን ያዘው። ከዚያ በኋላ ባቢሎን ለጊዜው የመስጴጦምያ ዋና ሥልጣን ሆነ።

የኢሲን ነገሥታት

ለማስተካከል

(ኡልትራ አጭር)