ኪሱራ
(ከኪሡራ የተዛወረ)
ኪሱራ የሱመር ጥንታዊ ከተማ ነበር። ዛሬው ሥፍራው ተል አቡ ሃታብ ተብሎ በዘመናዊው አገር ኢራቅ ውስጥ ይገኛል። ይህ ቦታ በሥነ ቅርስ መርማሪዎች ተቆፍሮ ብዙ ጽላቶች ተገኙበት።
ኪሱራ (ተል አቡ ሃታብ) | |
---|---|
ሥፍራ | |
ዘመን | 1850-1650 ዓክልበ. ግድም |
ዘመናዊ አገር | ኢራቅ |
ጥንታዊ አገር | ሱመር |
በ1850 ዓክልበ. ግድም ንጉሥ ኢቱር-ሻማሽ ከኢሲን መንግሥት ነጻነት ለከተማው ለኪሱራ መሠረተ። እንደ አገሩ ልማድ ለግዛቱ የራሱን የዓመት ስሞች አወጡ። በ1836 ዓክልበ. ግድም ተከታዩ ማናማልቴል ሆነ፤ እሱም የባቢሎን መጀምርያ ንጉሥ ሱሙ-አቡም እስከ ተነሣ ድረስ እስከ 1805 ዓክልበ. ድረስ በኪሱራ ነገሠ።
በ1776 ዓክልበ. የኢሲን ንጉሥ ኤራ-ኢሚቲ ኪሱራን ያዘ። በ1715 ዓክልበ. ደግሞ የላርሳ ንጉሥ ሪም-ሲን ኪሱራን ወደ ግዛቱ ጨመረው። በ1650 ዓክልበ. የባቢሎን ንጉሥ ሳምሱ-ኢሉና ኪሱራን አጠፋ።