ኢዲን-ዳጋን
ኢዲን-ዳጋን ከ1862 እስከ 1850 ዓክልበ. ግድም ድረስ (ኡልትራ አጭር አቆጣጠር) ከኢሲን ሥርወ መንግሥት የሱመር ንጉሥ ነበር። ማዕረጉ በይፋ «የኡር፣ የሱመርና የአካድ ንጉሥ» ነበረ።
የሱመር ነገሥታት ዝርዝር ኢዲን-ዳጋን ለ፳፩ ዓመታት እንደ ገዛ ሲለን፣ ፲፫ የዓመት ስሞች ብቻ ለእርሱ ይታወቃሉ። ፪ኛው ዓመት «የኢዲን-ዳጋን ሴት ልጅ ማቱምኒያቱም የአንሻንን ንጉሥ ያገባችበት ዓመት» ተባለ። ከዚህ በቀር፣ የዓመት ስሞቹ ለአረመኔ ጣኦታቱ ሥርዓት ጌጣጌጥ ወይም ሕንጻዎች ስለ መሥራቱ ናቸው እንጂ ምንም ዘመቻ ወይም ፖለቲካዊ ጉዳይ አይዘግቡም። [1] በዚህ ዘመን አለቆቹ በቅንጦት እንደ ኖሩ ይሆናል።
ኢዲን-ዳጋን ከአሞራውያን ዘር ቢሆንም አሞራውያን ሱመርን ከማስቸግር አልቀሩም። በአንድ ጽላት ቅጂ ዘንድ፣ የኢዲን-ዳጋን ሻለቃ ሲን-ኢላት ከአሞራውያን ነገድ ጋር በካኩላቱም ዙሪያ ተዋጋ። የአሞራውያን አለቃ ምናልባት ሳሚዩም ነበረ፤ ልጁም ጉንጉኑም በኋላ (1844 ዓክልበ. ግድም) በላርሳ ነጻነት አዋጀ። የኢዲን-ዳጋን ሥልጣን በኒፑር ላይ ደግሞ ለጊዜው እንደ ጠፋ ይቻላል። በኋላ ዘመን የኢሲን ንጉሥ ኤንሊል-ባኒ እንደ ዘገበው፣ ኢዲን-ዳጋን ፪ የጣኦት ሐውልቶች ሠርቶ ወደ ኒፑር ግን ሊያስገባቸው አልቻለም፤ ሐውልቶቹም እስከ ኤንሊል-ባኒ ዘመን ድረስ በኢሲን ቆዩ። እንዲሁም የኢዲን-ዳጋን ልጅና ተከታይ እሽመ-ዳጋን ኒፑርን ወደ ኢሲን ግዛት እንደ መለሠው ይባላል።[2]
ሌላ ጽላት እንደ አረምኔ እምነታቸው ንጉሥ ኢዲን-ዳጋን በሰዶማዊ ሠልፍ እንደ ታየ ይናገራል።[3] እስከምናውቅ ድረስ ይሄ በታሪክ መጀመርያው በአንዱ መንግሥት የተደገፈው ሰዶማዊ ሠልፍ የተከሠተበት ጊዜ ይመስላል።
ቀዳሚው ሹ-ኢሊሹ |
የኢሲንና የሱመር ንጉሥ 1862-1850 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ እሽመ-ዳጋን |
- ^ የኢዲን-ዳጋን ዓመት ስሞች
- ^ የላርሳ ንገሥታት Archived ኦክቶበር 21, 2012 at the Wayback Machine pp. 32-34 (እንግሊዝኛ)
- ^ የኢዲን-ዳጋን አረመኔ ሥነ ሥርዓት