ኡር-ኒኑርታሱመርኢሲን ሥርወ መንግሥት 6ኛው ንጉሥ ነበረ (1823-1806 ዓክልበ. የነገሠ)።

በንጉሥ ሊፒት-እሽታር ውድቀት ዙፋኑን ያዘ። መጀመርያ ፭ የኢሲን ነገሥታት ሴማዊ (አሞራዊ) ስሞች ሲኖራቸው፤ «ኡር-ኒኑርታ» ግን ሱመርኛ ስም ነው።

ሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ላይ ፳፰ ዓመታት እንደ ነገሠ ሲለን ከዘመኑ ፲፭ የዓመት ስሞች ብቻ ይታወቃሉ።[1] ከመጀመርያው ዓመቱ በቀር ግን የሌሎቹ ዓመታት (a-n) ቅድም-ተከተላቸው እርግጥኛ አይደለም። ከነዚህም መካከል ለምሳሌ፦

፩ ፦ (1823 አክልበ. ግድም) «ኡር-ኒኑርታ ንጉሥ የሆነበት ዓመት»
a ፦ «የኒፑር ዜጎች ለዘላለም ነጻ ያወጣቸውበት፣ በአንገታቸውም የሸከመውን ግብር የፈታላቸውበት ዓመት»

በአንዱ ዓመቱ (a) ኡር-ኒኑርታ ኒፑርን ከኢሲን ተወዳዳሪ ከላርሳ ግዛት እንዳስመለሰ ይመስላል። በ1809 ዓክልበ. የላርሳ ንጉሥ አቢሳሬ ኢሲንን እንዳሸነፈው ከራሱ ዓመት ስም ይታወቃል። ከዚህ በቀር ኡር-ኒኑርታ መስኖ እና ቦይ በማስቆፈሩ አሮንቃ ምድርን አስደረቀ።

በዚህም ዘመን ሌሎች ነጻ ከተሞች የራሳቸውን ነገሥታትና ዓመት ስሞች ነበራቸው። የኢሊፕ-አኩሱም ንጉሥ ሃሊዩም ዓመት ስም (a) እና የኪሱራ ንጉሥ ማናባልቴኤል ዓመት ስም (g) ሁለቱም «ኡር-ኒኑርታ የተገደለበት ዓመት» ይባላሉ፤ ይህም 1806 ዓክልበ. ይሆናል። ልጁ ቡር-ሲን ተከተለ።

ቀዳሚው
ሊፒት-እሽታር
ኢሲን ንጉሥ
1823-1806 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ቡር-ሲን

ዋቢ ምንጮች

ለማስተካከል
  1. ^ የኡር-ኒኑርታ ዓመት ስሞች