ሱሙ-አቡም ከ1807 እስከ 1793 ዓክልበ. ድረስ (ኡልትራ አጭር) የባቢሎን መጀመርያ ንጉሥ ነበረ።

በዚህ ወቅት የኢሲንና የላርሳ መንግሥታት ለሱመርና ለአካድ ላዕላይነት ሲወዳደሩ ብዙ ነጻ ከተማ-አገሮች ወደ ስሜን ተነሡ። ከነዚህ መካከል አንዱ ካዛሉ ሲሆን አሞራዊው ሱሙ-አቡም በ1807 ዓክልበ. ግድም የባቢሎን ነጻነት ከካዛሉ አዋጀ። ከዚህ በኋላ ከዓመት ስሞቹ ኢሊፕ (የ«ማናና» መንግሥት ከተማ)፣ ኪሽንና ካዛሉን ወደ ግዛቱ መጨምር እንደ ተቻለው ይመስላል።

ለዘመኑ ከ፲፬ የዓመት ስሞቹ ሁላቸው በሙሉ ታውቀዋል። ከነርሱም መካከል፦

1807 ዓክልበ. ግ. - «ሱሙ-አቡም ንጉሥ የሆነበት ዓመት» / «የባቢሎን ታላቅ ግድግዳ የተሠራበት ዓመት»
1805 ዓክልበ. ግ. - «የኢሊፕ ከተማ ግድግዳ የተያዘበት ዓመት»
1798 ዓክልበ. ግ. - «የኪሽ ግድግዳ የሠራበት ዓመት»
1795 ዓክልበ. ግ. - «ሱሙ-አቡም ካዛሉን ያጠፋበት ዓመት»

የሱሙ-አቡም ተከታይ ሱሙላኤል ነበረ።

ቀዳሚው
የለም (አዲስ)
ባቢሎን ንጉሥ
1807-1793 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሱሙላኤል

የውጭ መያያዣ ለማስተካከል