አሦር
አሦር (አሹር) ማለት በጥንታዊ ዘመን በላይኛ ጤግሮስ ወንዝ አጠገብ የተገኘ ከተማና አካባቢው ነበረ። በኋለኛ ጊዜ የአሦር መንግሥት ሃይለኛ ሆኖ መላ መሬት እስከ ግብጽ ድረስ ገዛ። በጥንታዊ አሦር ከተማና በጤግሮስ አጠገብ ያሉትም ተራሮች እስከ ዛሬው አርሜንያ ድረስ 'የአሦር ተራሮች' ይሰየሙ ነበር።
በኦሪት ዘፍጥረት መሠረት አሦር (አሹር) ከኖኅ ልጅ ሴም ልጆች አንዱ ሲሆን፥ ከሰናዖር ወጥቶ አንዳንድ ከተማ ሠራ። በአሦራውያንም እምነት ዘንድ 'አሹር' ከተማውን የመሠረተው አምላክ ስም ነበረ።
ከቅድመኛው ዘመን አውራጃው ሹቡር ተብሎ ከሰናዖር (ሹመር)፣ ማሪ ወይም ከአካድ ይገዛ ነበር። ሹቡር በታላቁ ሳርጎን መንግሥት ውስጥ ክፍል ሆኖ ጉታውያን እስከ አጠፉት ድረስ ቆየ። በኋላ እስከ 1879 ዓክልበ. ግ. ከኡር 3ኛ ሥርወ መንግሥት ይቆጣጠር ነበር። የዑር መንግሥት ሲወድቅ የአሦር ከተማ ነገሥታት ሊሙ ስሞች ይመዘገባሉ።
በዚህ ወቅት አሦር ከተማ-አገር ብቻ ነበረ። ሆኖም አሦራውያን የብረታብረት ንግዳቸውን ለማስፋፋት በማሰብ አንዳንድ ቅኝ-ከተማ (ካሩም) በሐቲ (ዛሬው ቱርክ) ውስጥ መሠረቱ። ከነዚህም ዋነኛው ካነሽ የተባለው ከተማ ነበር።
በ1720 ዓክልበ. ግ. አሞራዊው ንጉሥ 1 ሻምሺ-አዳድ አገሩን ከነአሦር ከተማ አቀና። ልጁን 1 እሽመ-ዳጋን (1688-1678 ዓክልበ.) በአሦር ላይ ሾመው። ነገር ግን የባቢሎን ንጉስ ሃሙራቢ ድል አድርጎት ዙሪያው ወደ ባቢሎን መንግሥት ተሳለፈ። ከትንሹ እስያ ይካሄድ የነበረው የብረታብረት ንግድ በዚያን ጊዜ ተቋረጠ። ለሚከተለው መቶ አመት አሦር ለባቢሎን ተገዥ ነበር።
በ1507 ዓክልበ. ግ. ባቢሎን ለካሣውያን ከወደቀ በኋላ፥ አሦር በሚታኒ መንግሥት (ሑራውያን) በ1441 ዓክልበ.ግ. ይሸነፍ ነበር። ሚታኒ በኬጢያውያን ግፊት ሲወድቅ ግን የአሦር ንጉስ አሹር-ኡባሊት ነጻነቱን አዋጀ (1366 ዓክልበ. ያህል)። ከዚህ በላይ ይህ አሹር-ኡባሊት የራሱን ልጅ ኩሪጋልዙን በባቢሎን ዙፋን ላይ አሾመው።
በ1290 ዓክልበ. የአሦር ንጉስ 1 አዳድ-ኒራሪ የሚታኒን መንግሥት አሸነፈ። የአዳድ-ኒራሪ ተከታይ 1 ስልምናሶር መንግሥቱን በከጢያውያን አግጣጫ እስከ ከርከሚሽ ድረስ አስፋፋ። የስልምናሶርም ልጅ 1 ቱኩልቲ-ኒኑርታ እንኳን በባቢሎን ላይ ገዛ። ሆኖም በቅርብ ጊዜ ባቢሎን በአሦር ላይ አመጽ ታደርግ ነበር።
በ1200 ዓክልበ.. አካባቢ የኬጢያውያን መንግሥት በሙሽኪ (ፍሩጋውያን) ግፊት ስለ ወደቀ፥ ባቢሎንና አሦር ለአሞራውያን መሬት ተወዳዳሪዎች ሆኑ። የአሦር ንጉስ 1 አሹር-ረሽ-ኢሺ በዚህ አቅራቢያ በ1140 ዓክልበ. በባቢሎንን ንጉሥ 1 ናቡከደነጾር ላይ አሸነፈ።
የአሹር-ረሽ-ኢሺ ልጅ 1 ቴልጌልቴልፌልሶር የመንግሥቱን ጠረፍ በጣም አስፋፋ። ከርከሚሽን ከመማረኩ በላይ በሙሽኪ ላይ እስከ ጥቁር ባሕር ድረስ ዘመቻ አደረገ። ደግሞ እስከ ሜድትራኒያን ባሕር ድረስ ሲዘረጋ ፊንቄን (ሊባኖስ) ያዘ።
ከ1 ቴልጌልቴልፌልሶር በኋላ ከጎረቤቶቹ ከአራማውያንና ከኡራርቱ የተነሣ የአሦር ኅይል ደክሞ ነበር። በ920 ዓክልበ. ግን 2 አዳድ ኒራሪ ንጉሥ ሆሞ የአሦር ሃይል ታደሰ። ደግሞ ወደ ስሜን የኖሩትን ሕዝቦች በሙሉ በሰፈራ አፈለሳቸው። ይሁንና መንግሥቱ ከአቦር ወንዝ ወደ ምዕራብ አልዘረጋም።
ንጉስ አሹር-ናሲር-ፓል ከ890 ዓክልበ. ጀምሮ ነግሦ ያለ ምኅረት ጠረፎቹም አስፋፋ። ከአቦርና ከኤፍራጥስ መካከል ያሉትን አራማውያን ድል አድርጎ በሜድትራኒያን ሲደርስ ፊንቄን ቀረጠ። ካልሁንም ዋና ከተማው እንዲሆን አደረገው።
በልጁ 3 ስልምናሶር 34 አመት ዘመን (865-831 ዓክልበ.) አሦር በየአመቱ ለጦርነት ሠለፈ። ባቢሎን ተወርሮ ተቀረጠ። የሶርያ (አራም-ደማስቆ) ንጉስ ወልደ አዴር (አድርአዛር) ከእስራኤል ንጉስ አክዓብ ጋራ በቃርቃር ፍልሚያ ስልምናሶርን አጋጠመው። ስልምናሶርም ፊንቄንና የእስራኤል ንጉስ ኢዩን አስቀረጠ። በዋና ከተማው በካልሁ የተገኘው ጥቁር ሐውልት ስለ 3 ስልምናሶር ዘመን ድርጊቶች ይመሰክራል [1]። ከዚህ ቀጥሎ የአሦር አቅም ለመቶ አመት እንደገና ይደክም ጀመር። ሆኖም ንጉሱ 3 አዳድ-ኒራሪ (818-790 ዓክልበ.) ስርያን ማረከ ሜዶንንም ወረረ።
3 ቴልጌልቴልፌልሶር
ለማስተካከልበ755 ዓክልበ. አሦር በብሔራዊ ጦርነት ተይዞ ባቢሎን በንጉሱ ናቦፖላሣር መሪነት እንደገና ነጻነቱን አዋጀ። በሚከተለው አመት ፎሐ (ፑሉ) የሚባል አለቃ የአሦር መንግሥት ቀምቶ 3 ቴልጌልቴልፌልሶር ተብሎ ንጉስ ሆነ። እሱ በዘመኑ ባቢሎንን ዳግመኛ ቀርጦ ኡራርቱን፤ ሜዶንንና ኬጢያውያንን ድል አድርጎ ሠራዊቱን ወደ ሶርያ ወደ ፊንቄም አዞረ። አርፋድን በ 748 ዓክልበ. አጠፋ፤ ሐማትንም ያዘ። በ746 ዓክልበ. ፊልሥጥኤም ወርሮ የእስራኤልን ንጉስ ምናሔምን 1000 መክሊት ብር አስገበረ። በኋላ (740 ዓክልበ.) የእስራኤል ንጉስ ፋቁሔ ከሶርያ (አራም) ንጉስ ረአሶን ጋራ አደጋ በይሁዳ ላይ ሲጣሉ የይሁዳ ንጉሥ አካዝ የመቅደሱን ወርቅ ሰጥቶ ከቴልጌልቴልፌልሶር እርዳታ ጠየቀ። ከዚያ ቴልጌልቴልፌልሶርም ደማስቆን አጠፍቶ የሶርያ ሕዝብና የእስራኤል ግማሽ ሕዝብ በምርኮት ወደ ሌላ አገሮች ሰደዳቸው።
በ737 ክ.በ. ቴልጌልቴልፌልሶር ወደ ባቢሎን ወርዶ ንጉሱን ናቡ-ሙኪን-ዜሪ ማረከና እራሱ 'የባቢሎን ንጉስ ፑሉ' ተብሎ ዘውዱን ተጫነ።
5 ስልምናሶር
ለማስተካከልበ735 ክ.በ. ልጁ 5 ስልምናሶር ተከተለው። እሱ የመንግሥቱን ግዛት በየአውራጃው እያካፈለ፣ ተገዥ አገሮች ቀረጥ አንሰጥም ብለው አመጸኛ በሆኑበት ወቅት፣ አሦራዊ አገረ ገዥ አደረገባቸው። የእስራኤል ንጉሥ ሆሴዕ ግን በ733 ክ.በ. ግብርን ባቋረጠ ጊዜ የግብጽ ጠባቂነት አገኘ። ስለዚህ ስልምናሶር ወርሮ ከሦስት አመት ትግል በኋላ ሰማርያን ያዘና የእስራኤልን ቅሬታ ወደ ሌላ አገሮች ሰደዳቸው።
2 ሳርጎን
ለማስተካከልበ730 ክ.በ. ስልምናሶር ሰማርያን እየከበባት ድንገት ከሞተ በኋላ ሻለቃው 2 ሳርጎን ዙፋኑን ያዘ።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |