ኦሪት ዘፍጥረትመጽሐፍ ቅዱስ፣ የብሉይ ኪዳንና የኦሪት የመጀመሪያው መፅሐፍ ነው።

በዚሁ መጽሐፍ ከሥነ-ፍጥረትየዔድን ገነት ጀምሮ እስከ ዮሴፍ ዕረፍት በጌሤም ድረስ ይተረካል። በተለይ ለአብርሃም፣ ለወላጆቹና ለተወላጆቹ ትኩረት ይሰጣል።

በልማድ መሠረት፣ እንደ ሌሎቹ የኦሪት መጻሕፍት፣ የመጽሐፉ ደራሲ ወይም አቀነባባሪ ሙሴ እንደ ነበር ይባላል። እንዲሁም ሌላው መጽሐፍ፣ መጽሐፈ ኩፋሌ ስለነዚህ ታሪኮችና ዘመኖች ሲተርክ፣ መላዕክት ለሙሴ በደብረ ሲና በቀጥታ እንዳቀረቡት ይላሉ። በኦሪት ዘፍጥረት ውስጥ ካለው መረጃ፣ ግማሹ ያህል ከኩፋሌ ውስጥ ደግሞ ይገኛል። በዘፍጥረት ውስጥ ሌላው ግማሽ ካልታወቁት ምንጮች ወይም ጥንታዊ ልማዶች ሊሆኑ ይቻላል።

: