ነሐሴ ፲፪
(ከነሐሴ 12 የተዛወረ)
ነሐሴ ፲፪ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፵፪ ኛው ቀን ሲሆን የክረምት ወቅት ፵፯ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፳፬ ቀናት ሲቀሩ፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፳፫ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፱፻፱ ዓ/ም - በግሪክ ሁለተኛ ከተማ በተሰሎንቄ (Thessaloniki) የተከሰተ የእሳት አደጋ የከተማዋን ቤቶች በቁጥር ከሦስት እጅ አንድ በማውደሙ እስከ ፸ሺ ነዋሪዎችን ውጭ አዳሪ ቤት አልባ አድርጓቸዋል።
- ፲፱፻፳፩ ዓ/ም - ከፈረንሳይ የተገዛ 'ፖቴዝ' ባለ ሁለት ሞተር የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አየር ዠበብ አዲስ አበባአረፈ። ሁለተኛው አየር ዠበብ፣ ከአለማኒያ የተገዛው 'ጁንከርስ' አየር-ዠበብ ወዲያው አከታትሎ ገብቷል።
- ፲፱፻፶፮ ዓ/ም - የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ(International Olympic Committee - IOC) ዘረኛውን የደቡብ አፍሪቃ መንግሥት ‘አፓርታይድ’ በሚል መርሆ የሚያካሂደውን የግፍ አስተዳደር እንዲያወግዝ ያቀረበለትን ጥሪ ባለመቀበሉ በዚህ ዓመት ቶክዮ ከተማ ላይ በተዘጋጀው ፲፰ኛው የኦሊምፒክ ውድድር ላይ እንዳይሳተፍ አገደው።
ልደት
ለማስተካከል- ፲፰፻፴፮ ዓ/ም - ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ደብረ ብርሃን አካባቢ አንጎለላ ላይ ተወለዱ።
ዕለተ ሞት
ለማስተካከልዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- (እንግሊዝኛ)Pankhurst,Richard; A Short History of Aircraft in Ethiopia (2012);Pankhurst's Corner: http://www.capitalethiopia.com
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |