ነሐሴ ፳፭
በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፶፭ ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነሉቃስ ፲፩ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ ማርቆስ እና ዮሐንስ ደግሞ ፲ ዕለታት ይቀራሉ።
፲፱፻፵፱ ዓ/ም የቀድሞዋ ማላያ (የአሁኗ ማሌዢያ) ነጻነቷን ከብሪታንያ ተቀዳጀች።
፲፱፻፶፬ ዓ/ም ትሪንዳድ እና ቶባጎ የሚባሉት የካሪቢያ ባሕር ደሴቶች ነጻነታቸውን ከብሪታንያ ተቀዳጁ።
፲፱፻፹፫ ዓ/ም የኪርጊዝስታን ሪፑብሊክ ከሶቪዬት ሕብረት ሥር ነጻ ወጣች።
፲፱፻፹፬ ዓ/ም በኮንጎ ሪፑብሊክ በተካሄደው ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ፓስካል ሊሱባ በፕሬዚዳንትነት ተመረጡ።
፲፱፻፹፱ ዓ/ም የብሪታንያ አልጋ ወራሽ የልዑል ቻርልስ ባለቤት ዲያና የዌልስ ልዕልት በመኪና አደጋ ፓሪስ ከተማ አረፉ።
፳፻ ዓ/ም በመሐንዲስ ኃይሉ ሻውል የሚመራው መስከረም ፲፬ ቀን ፲፱፻፺፰ ዓ/ም የተዋሐደው ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ስሙን በመለወጥ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ተብሎ ተሰየመ፡፡
ልደት
ለማስተካከልዕለተ ሞት
ለማስተካከል፲፱፻፷፩ ዓ/ም የዓለም የከባድ ሚዛን የቡጢ ውድድር መደብ ቻምፒዮና የነበረው ኢጣልያ አሜሪካዊው ሮኪ ማርሲያኖ አረፈ።
፲፱፻፹፱ ዓ/ም የብሪታንያ አልጋ ወራሽ የልዑል ቻርልስ ባለቤት ዲያና የዌልስ ልዕልት በመኪና አደጋ ፓሪስ ከተማ አረፉ።