ቺ ዮው
ቺ ዮው በቻይና፣ በና በህሞንግ አፈ ታሪክ በኩል ጥንታዊ ንጉሥ ነበረ።
በትውፊቱ መሠረት ቺ ዮው 2365 ዓክልበ. ግድም የሊ ወገን ንጉሥ ሲሆን የያንዲና የኋንግዲ ጠላት ሆነ። ሦስት ውግያዎች ተከተሉ። በመጀመርያው የቺ ዮው ሥራዊት ያንዲውን አሸነፈው። ከዚያ ያንዲው ተሸንፎ ወደ ኋንግ ዲ (ወደ ዥዎሉ) ሸሸ። በሁለተኛው የዥዎሉ ውግያ ኋንግ ዲ እና ቺ ዮው ተጋጠሙ። በዚህ ውግያ ቺ ዮው ጉምን በጥንቆላ ፈጥሮ ኋንግ ዲ እንደገና በተነው፣ ብዙም ሌሎች ጉድ ሥራዎች እንደ ተከሠቱ የሚል ወሬ አለ።
በቻይና መዝገቦች ዘንድ፣ ቺ ዮው በዚህ ውግያ ድል ሆነ። በኮርያ መጻሕፍት ግን ቺ ዮው («ጃውጂ ኋኑንግ» ተብሎ) በዚህ ውግያ ድል አደረገ፣ ደግሞ የሺንሺ ንጉሥ ይባላል። በቻይና ሃይማኖት ደግሞ ከ200 ዓክልበ. እስከ 65 ዓ.ም. ግድም ድረስ ቺ ዮው እንደ ጦርነት አምላክ ይቆጠር ነበር።