ዥዎሉ (ቻይንኛ፦ 涿鹿) የቻይና ከተማ ነው።
40°22′ ሰሜን ኬክሮስ እና 115°12′ ምሥራቅ ኬንትሮስ
በቻይና ልማዳዊ አፈ ታሪክ ዘንድ፣ ዥዎሉ በቻይና ጥንታዊው ንጉሥና ቅድማያት ኋንግ ዲ («ቢጫው ንጉሥ») ተመሠርቶ እንደ ዋና ከተማው አገለገለው። በተጨማሪ በዚህ አካባቢ በዥዎሉ ውግያ (2331 ዓክልበ. ግድም) ኋንግ ዲ ጠላቱን ቺ ዮውን ድል አደረገው።