ተረት ሸ
- ሸማ ለብሶ ስልቻ በቅሎ ጭኖ ለብቻ
- ሸማ ማዋስ ለባላገር በቅሎ ማዋስ ለወታደር
- ሸማ በውሀ ሰው በንስሀ
- ሸማን በውሀ ሰውነትን በንስሀ
- ሸማ በየፈርጁ ይለበሳል
- ሸማና ምስጥ ወደ ውስጥ
- ሸማኔ በመኑ ጠይብ በከሰሉ
- ሸማኔ በድሩ ጠይብ በመንደሩ
- ሸማኔ ድውሩን ባለስልጣን ክብሩን
- ሸማን ጠምዞ ያሰጧል እህልን አላምጦ ይበሏል
- ሸምበቆ በመርዘሙ አይሆንም ምሰሶ
- ሸምበቆ በመርዘሙ ምሰሶ አይሆንም
- ሸርሙጣ ስታረጅ አቃጣሪ ትሆናለች
- ሸርሙጣን የወደደ ልብሱን ጥሎ አበደ
- ሸርሙጣን የወደደ ልብሱን ጥሎ ያበደ
- ሸኚና ጥላ ቤት አይገባም
- ሸኚ ቤት አያደርስም
- ሸኝ ቤት አይገባም
- ሸክላ ቢጥሉት ገለባ
- ሹመት ላወቀው ይከብደዋል ላላወቀው ያሳብደዋል
- ሹመት ሲገኝ ዘመድ አይገድም
- ሹመት ሺህ ሞት
- ሹመት በተርታ ስጋ በገበታ
- ሹመት የለመደ ወንዝ ዳር ይወርዳል
- ሹመትና ቁመት ከልኩ አያልፍም
- ሹመትና ቁመት አይገኝም በምኞት
- ሹም ለመነ አዘዘ
- ሹም ለሹም ያወርሳል ጉም ተራራ ያለብሳል
- ሹም ለሹም ይጎራረሳል ድሀ ለድሀ ይለቃቀሳል
- ሹም መክሰስ ወጀድ ማረስ አይቸግርም
- ሹም ሲቆጣ ማር ይዞ እደጁ ደስ ሲለው ማር ይዞ እደጁ
- ሹም ቢሞት ሀምሳ የሹም ልጅ ቢሞት መቶ ሀምሳ
- ሹም ቢሞት ቀባሪው ሀምሳ የሹም ልጅ ቢሞት መቶ ሀምሳ
- ሹም ያዛል ቄስ ይናዝዛል
- ሹምና ማር እያደር ይከብዳል
- ሹምና የጋማ ከብት በጊዜ ይከተት
- ሹምና ጥጥ እያደር ይከብዳል
- ሹምና ጥጥ እያደር ይከዳል
- ሹሩባ ትሰራ ሄዳ ጠጉሩዋን ተላጭታ መጣች
- ሹክሹክታ የጠብ ወለምታ
- ሺ መት ሺ ሞት
- ሺም ታለበ አንድ ያው በገሌ
- ሺ በመከረ አንድ በወረወረ
- ሺ በመከር አንድ በወረወር
- ሺ አውል ሲሞት ሺህ ይሙት
- ሺ አውል ከሚሞት ሺ ይሙት
- ሺ አውል ኪሞት ሺ ይሙት
- ሺ ይሙቱ ሺ አውል አይሙት
- ሺ ዝንብ መሶብ አይከፍትም
- ሺህ ቢታለብ አንድ በገሌ አለች ድመት
- ሺ ቢታለቡ ከገሌ አላልፍም አለች ድመት
- ሺ ቢያጩሽ አንድ ያገባሽ
- ሺ ያጭሽ አንድ ያገባሽ
- ሻማ ራሱ ነዶ ራሱ ብርሀን ይሰጣል
- ሻሽ ይደምቃል ማቅ ይሞቃል የሚበጀውን ባለቤቱ ያውቃል
- ሻጭ ገዥ ሆኖ ይገምታል
- ሽልም እንደሆን ይገፋል ቂጥም እንደሆን ይጠፋል
- ሽል ከሆነ ይገፋል ቂጣም ከሆነ ይጠፋል
- ሽል እንደሆን ይገፋል ቂጣም እንደሆን ይጠፋል
- ሽመልና ዘንግ ቂልና በግ
- ሽማግሌ ሳለ ምክር አይጠፋም ጎልማሳ ሳለ ላም አይነዳም
- ሽማግሌ በምክሩ አርበኛ በሰናድሩ
- ሽማግሌ ካለበት ነገር አይናቅበት
- ሽማግሌ ካለበት ነገር አይሰረቅ ጎበዝ ካለበት በትር አይነጠቅ
- ሽማግሌ ካልሞተ ስንዴ ካልመረተ
- ሽማግሌ ካልሞተ ስንዴ ካልሸተ
- ሽማግሌ ይገላግላል የተጠቃ አቤት ይላል
- ሽማግሌና ስልቻ ሳይሞሉ አይቆሙም
- ሽማግሌና ጅብ በላላባት ይገባል
- ሽማግሌን ከምክር ከመለየት ከምግብ መለየት
- ሽሮን ሲሸውዷት ፕሮቲን ነሽ አሏት
- ሽሽት ከኡኡታ በፊት
- ሽበት ምን ታረግ መጣህ ቢሉት እኖር ብዬ አለ
- ሽበት እኖር ብዬ መጥቻለሁ አለ
- ሽታና ግማት ላልሰማ ማውራት
- ሽንብራ መኖር በመከራ
- ሽንኩርት አንድም በሉት ገማ ደገሙትም ገማ
- ሽንኩርት የባህሪውን ይሸታል
- ሾላ በድፍን
- ሾተልን ወደ ሰገባህ ቁጣህን ወደ ትእግስት
- ሾተልን ወደ አራዊት ቁጣህን ወደ ትእግስት
- ሾተልን ወደ አፎት ቁጣን ወደ ትእግስት
- ሽሮ ቢደነፋ እንጀራ እስኪቀርብ ነው