ተረት መ
- መሄድ በጋ ነው መቀመጥ ክረምት ነው
- መሄጃ የሌለው መውጫውን ያበስራል
- መልከ ጥፉ በስም ይደግፉ
- መልከ ጥፏ ቆንጆዋን አስናቀች
- መልካም ባል መጥፎ ሴት ይገራል
- መልካም ሴት ለባሏ ዘውድ ናት
- መልካም ስም ከመቃብር በላይ ይውላል
- መልካም ስም ከመቃብር በላይ ይቆማል
- መልካም አባት ለልጆቹ እጁን ኪሱ ይከታል
- መልካም ባል መጥፎ ሴት ይገራል
- መልኳ ባያምር አመሏ ይመር
- መልክ ታጥቦ አይጠጣ ወይ አይበላ
- መልክ ስጠኝ እንጂ ሙያ ከጎረቤቴ እማራለሁ
- መመራመር ያገባል ከባህር
- መሞት የፈለገ ግልገል ቀበሮ ቤት ሄዶ ይጨፍራል
- መራጭ ይወድቃል ከምራጭ
- መቀመጥ በአልጋ ታላቅ ደጋ
- መቅረቧን ሳታውቅ እጇን ታጠበች
- መብላቷን ሳታውቅ እጇን ታጠበች
- መተው ነገሬን ከተተው
- መቼ መጣሽ ሙሽራ መቸ ቆረጠምሽ ሽንብራ
- መካር የሌለው ንጉስ አለ አንድ አመት አይነግስ
- መንገድ ካገር ልጅ ምክር ከጨዋ ልጅ
- መወለድ ቋንቋ ነው
- ሚስቱ ክፉ ባቄላ እራቱ ብሳና እንጨቱ ሀዘን ነው እቤቱ
- ሚስቱ ደግ ስንዴ እራቱ ወይራ እንጨቱ ደስታ ነው እቤቱ
- ሚስቱን ጠልቶ ካማቱ ልጁን ከሶ ካባቱ
- ሚስቱን ገድሎ አማቱ ቤት ተሽሽገ
- ሚስት ባታብል ባሏን ትወልዳለች
- ሚስት ከፈቷት ባዳ ማሽላ ከተቆረጠ አገዳ
- ሚስትህ አመዳም ጎራዴህ ጎመዳም
- ሚስትህ አረገዘች ወይ ቢለው ማንን ወንድ ብላ አለው
- ሚስትህን ስደድ በሬህን እረድ ይላል የባለጌ ዘመድ
- ሚስትና ዳዊት ከብብት
- ሚስት ፈትቶ ካማት መቀለብ በእንፉቅቅ መሄድ
- ሙቅ ውሀና የሰው ገንዘብ አይጠቅምም
- ሚስጥርህን ለባእድ ለምን አዋየኸው ወንፊት ወሀ ይዞ የት ሲደርስ አየኸው
- ማሞ ሌላ መታወቂያው ሌላ
- ማር በበላሁበት በጣፈጠው አፌ ጎመን ጎረስኩበት አይ አለማረፌ
- ማሽላ ሲያር ይስቃል
- ማሽላ እየፈካ ያራል
- ማቅ ይሞቃል ጋቢ ይደምቃል ገቢውን ባለቤት ያውቃል
- ማን ሙሽራ ቢልሽ ትኳያለሽ
- ማን ያውራ የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ
- ማን ያውራ የነበረ ማን ይጨፍር የሰከረ
- ማእድ ጠፋና አንድ ላይ በላን
- ማግባቱ ቀርቶብኝ በታጨሁ
- ማጣት ከሰማይ ይርቃል
- ምላጭ ቢያብጥ በምን ይበጡ ውሀ ቢያንቅ በምን ይውጡ
- ምን ያመጣ ድሀ ምን ያገሳ ውሀ
- ምን ቢያርሱ እንደጎመን አይጎርሱ
- ምንም ቢጠም መንገድ ምንም ቢከፋ ዘመድ
- ምን ቢፋቀሩ አብረው አይቀበሩ
- ምከረው ምከረው እንቢ ካለህ መከራ ይምከረው
- ሞት በጥር በነሀሴ መቃብር
- ሞት ቢዘገይ ሲኦል ስለሞላ ነው
- ሞት ቢዘገይ ነው የምሄደው
- ሞት ቢዘገይ የቀረ ይመስላል
- ሞት የሰጠው ቀባሪ አያሳጣውም
- ሞኝ ሲስቁበት የሳቁለት ይመስለዋል
- ሞኝ እከኩን እያየች ስትስቅበት ወደደችኝ ብሎ ይፈነድቃል
- ሞኝና ወረቀት ሊደራደሩ ነው
- ሞኝና ወረቅት ኢንተርኔትን ናቁ
- ሞኝና ወረቅት የያዘውን አይለቅም
- ሞኝ ውሀ ሲወስደው ይስቃል
- ሞኝ ዘመድ ከልጅህ እኩል አድርገኝ ይላል