ሰብታኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 10 መሠረት የኩሽ ሦስተኛ ልጅ ነበር።

በአንዳንድ ሊቃውንት ዘንድ፣ ሰብታ በአረቢያ ዳርቻ (በቀይ ባህር ላይ) ይገኝ የነበረው ሳቦታ በተባለ ሥፍራ ሰፈረበት። ይህ ሳቦታ የሃስረሞት ዋና ከተማ ነበረች።

ዳሩ ግን በ1ኛው ክፍለ ዘመን የጻፈው አይሁዳዊ መምህር ፍላቭዩስ ዮሴፉስ እንዳለው፣ «የሰብታ ልጆች ግሪኮች አሁን አስታቦራውያን የሚሏቸው ናቸው።» በጥንት «አስታቦራስ» ማለት አሁን በሱዳንና በኢትዮጵያ አትባራ ወንዝ የሚባል ስለ ሆነ፣ የሰብታ ኩሽ ልጆች በዚያ እንደ ሰፈሩ አመለከተ። በልማዳዊ መዝገብ የተወረሰው የኢትዮጵያ ነገሥታት ዝርዝር ደግሞ ሰብታ ለ30 አመታት በኩሽ መንግሥት ላይ ንጉሥ ሆነ ይላል፤ ይህም ከካም፣ ኩሽና ሃባሢ በኋላ ሲሆን አመቶቹ ሲቆጠር ምናልባት ከ2264 እስከ 2234 ዓክልበ. ይሆናል። አባ ጎርጎርዮስ እንዳሉ የሰብታ ሌላ ስም «አቢሲ» ስለ ሆነ ሀበሻ የሚለው ስም ከዚህ ነው። በነገሥታት ዝርዝሩ ግን ሰብታ የሀባሢ ተከታይ ይባላል። በሌላ ታሪክ መጽሐፍ ዘንድ፣ ሰብታ ወደ አባይ መነሻ ምንጭ ተጉዞ «በዚያው ቦታ ፱ በሮች የነበሩት ታላቅ ግንብ አስገንብቶ ወንድ በሽር ብሎ ሠየመው (ያሬድ ግርማ 1999 ዓም)።» በማለት ይጨምራል።[1] በዚያውም መጽሐፍ አቆጣጠር ዘንድ፣ ሰብታህ በቀጥታ ከአባቱ ከኩሽ ቀጥሎ ከ2545-2515 ዓክልበ. ነገሠ፤ ተከታዩም ኤለክትሮን የሰብታህ ልጅ ይለዋል። እንደገና በሌላ ታሪክ ዘንድ ሰብታህ በኩሽ የገዛ 2300 ዓክልበ. ግድም ሲሆን ይህ «ወንደ በሽር» ግንብ ዋና ከተማው ነበር[2]

አኒዩስ ቪተርቦ ባሳተመ በአንዱ አፈ ታሪክ ዘንድ፣ ይህ የኩሽ ልጅ ሰብታ (ወይም «ሳባትዮስ ሳጋ» ተብሎ) ከዚያ ዘመን በፊት በሳካዎች (እስኩቴስ) በአርሜኒያባክትሪያ ላይ የነገሠ ሲሆን፣ የመስጴጦምያ ንጉሥ ኒኑስ ከዚያ አባረረው። ከዚያም ዘመን በኋላ ከአፍሪካ ወደ ጣልያን ሂዶ በዚያው አገር ደቡብ ክፍል ነገሠ። ከዚህ በላይ ሳጉንቶ ከተማ በእስፓንያ እንደ መሠረተ የሚል ልማድ አለ።

ሌላ ሊቃውንት እንደሚያስቡት፣ በሞሮኮ ዳርቻ (በጂብራልታር ወሽመጥ ላይ) የሚገኘው ሴውታ የሰብታ ልጆች መኖራያ ይሆናል። ይህም የሴውታ ስያሜ በአረብኛ «ሰብታ» ስለ ሆነ ነው። ሆኖም የአረብኛው ከተማው ስም «ሰብታ» የመጣ ከሮማይስጥ ስያሜው «ሰፕታ ፍራትሬስ» (ማለት «ሰባት ወንድሞች»፣ ባካባቢው ስላሉ ፯ ኮረብቶች) ሲሆን፣ ከኩሽ ልጅ ሰብታ ጋር ግንኙነት እንዳለው አይመስልም።

ቀዳሚው
ስኩቴስ
ሳካዎች (እስኩቴስ) ንጉሥ
2320-2271 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ባርዛኔስ
ቀዳሚው
ሀባሢ
ኩሽ ንጉሥ
2264-2234 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ኤሌክትሮን
ቀዳሚው
ክራና ሄሌርና
የኩሬቴስ (ደቡብ ጣልያን) ኮሪቱስ
2250-2219 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ክራኑስ ራዜኑስ
  1. ^ የኢትዮጵያ ፭ ሺህ ዓመት ታሪክ ፍሥሐ ያዜ ካሣ፣ 2003-2005 ዓም፣ ገ. 32
  2. ^ «ቤተ እስራኤላዊያን በኢትዮጵያ ታሪካቸው ባህላቸውና አኗኗራቸው» ከመምህር አስረስ ያየህ አ.አ 1989 ዓ.ም