ፑዙር-ኤሽታር (ወይም ፑዙር-ኢሽታር) የማሪ ሻካናካ ወይም ገዥ ነበረ። ይህ ከ1922 እስከ 1897 ዓክልበ. ግድም ድረስ ነበር። የቱሪም-ዳጋን ልጅና ተከታይ ነበር።

የፑዙር-ዕሽታር ሐውልት

በተለይ የሚታወቀው በሥነ ቅርስ ስለ ሁለት ሐውልቶቹ ነው። ከአንድ ሰነድ ደግሞ ፩ኛው ዓመት የኡር ንጉሥ ሹልጊ ፵፬ኛው ዓመት መሆኑ ይታወቃል።

የፑዙር-ኤሽታር ልጅ ሒትላል-ኤራ በሻካናካነት ተከተለው።

ቀዳሚው
ቱራም-ዳጋን
ማሪ ሻካናካ
1922-1897 ዓክልበ.
ተከታይ
ሒትላል-ኤራ