ኒፑርሱመር ጥንታዊ ከተማ ነበር። በሱመራውያን ዘንድ የተቀደሰ ከተማ ሆኖ ይቆጠር ነበር። አረመኔ ቤተ መቅደስና ቄሳውንት ሲኖሩት ኒፑር የተገዛለት የሌላ ከተማ ንጉሥ የሱመር ላዕላይነት ማዕረግ ያገኝ ነበር። የቱማል ጽሑፍ ቅርስ እንደሚለን ይህን መቅደስ መጀመርያው የሠራው የኪሽ ንጉሥ ኤንመባራገሲ ነበረ። ከርሱ ቀጥሎ የኤንመባራገሲ ልጅ አጋ፣ የኡሩክ ንጉሥ ጊልጋመሽና ልጁ ኡር-ኑንጋል፣ የዑርም ንጉሥ መስ-አኔ-ፓዳና ልጁ መስኪአጝ-ኑና ሁላቸው በፈንታቸው የመቅደሱን ሥርዓት ያከብሩ ነበር። ከዚህ በኋላ ብዙ ሌሎች የሱመር ነገሥታት በኒፑር ተመረጡ።