ኢዲን-ኢሉም (ወይም ኢዲ-ኢሉም) በኡር መንግሥት ጊዜ በሹልጊ ዘመን የማሪ ሻካናካ ወይም ገዥ ነበረ። ይህ ከ1959 እስከ 1954 ዓክልበ. ግድም ድረስ ነበር።

የኢዲን-ኢሉም ሐውልት

በተለይ የሚታወቀው በሥነ ቅርስ ስለ አንድ ሐውልት ነው። ከጢሙ ጫፍ በቀር የሐውልቱ ራስ ጠፍቷል። በሐውልቱ የተቄረጹት ርጉም ቃላት እንዲህ ይላሉ፦ «ኢዲን-ኢሉም፣ የማሪ ሻካናካ፣ ይህን ሐውልቱን ለኢናና (አረመኔ ጣኦቷ) አስረክቧል። ማናቸውም ይህን ጽሑፍ የሚደምስስ፣ ኢናና ዘሩን ትደምስስ።»

የኢዲን-ኢሉም ልጅ ዚኑባ ስም ደሞ ከአንድ የሸክላ ማህተም ይታወቃል።

ቀዳሚው
አፒል-ኪን
ማሪ ሻካናካ
1959-1954 ዓክልበ.
ተከታይ
ኢሉም-ኢሻር