ጨው ማለት በጥንተ ንጥር ረገድ በተለይ NaCl (ሶዲየም ክሎሪድ) ነው። የተሠራው ከሶዲየም (Na) እና ክሎሪን (Cl) ንጥረ ነገሮች ነው። ይህ ማዕደን በምግብ ውስጥ ይበላል። ጣዕም ለመጨመር እንዲሁም የምግብን ኹኔታ ለማስጠበቅ በጣም ይጠቅማል።

ጨው
ጨው
ጨው

ጨው የምግብን ኹኔታ ስለሚያስቆይ፣ ሥልጣኔ በግብጽ ወዘተ. እንዲጀመር የጨው ጥቅም አይነተኛ ሚና ነበረው። ከጥቅሙ የተነሣ በ1 ወራት ውስጥ የሚበላሽ ምግብ እንግዲህ ከወራቱ በኋለ እንዲቆይ ተደረገ። ከዚህም በላይ፣ እንዲህ ያለ ምግብ በረጅም ጉዞ ላይ እንደ ሥንቅ መውሰድ ከዚያ ጀምሮ ተቻለ።

በጥንታዊ ዘመናት ጨው ዕጅግ ከፍ ያለ ዋጋ ስለነበረው በቻይናግሪክመካከለኛ ምሥራቅም ሆነ በአፍሪቃ ውድ የንግድ ቅመም ሆኖ ተቆጠረ። በሜዲቴራኔያን ዙሪያ እንዲሁም በሮማ መንግሥት፣ ጨው እንደ ገንዘብ (አሞሌ) አገለገለ። ይሁንና ሰዎች ጨው ከውቅያኖስ ጨዋማ ውሃ ማስገኘት በተማሩበት ጊዜ፣ የጨው ዋጋ ተቀነሠ። የፊንቄ ሰዎች ብዙ የውቅያኖስ ውኃ በየብስ ላይ አፍስሰው ውኃው ከተነነ በኋላ ጨውን አከማችተው ይሽጡት ነበር።

አንዳንዴ ደግሞ ጨው በጦርነት ጊዜ የከተማ ሰብል ለማበላሽ በእርሻ ላይ ተበትኖ እንደ ቅጣት መሣርያ ያገልግል ነበር። ለምሳሌ የአሦር ሰዎች ይህን በጎረቤቶቻቸው ላይ እንዳደረጉ በታሪክ መዝገቦች ይባላል።