ጳጉሜ ፮
ጳጉሜ ፮ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በወንጌላዊው ሉቃስ ስም በተሠየሙት እና በየአራት ዓመቱ በሚደገሙት ሰግር ዓመታት ብቻ የሚውል የዓመቱ የመጨረሻውና ፫፻፷፮ኛው ቀን ሲሆን የክረምት ወቅት ፸፩ኛው ቀን ነው።
በቅርብ ዘመናት ጳጉሜ ፮ ከዋለባቸውና ወደፊትም ከሚውልባቸው ሰግር ዓመታት፤ ፲፱፻፷፫፣ ፲፱፻፷፯፣ ፲፱፻፸፩፣ ፲፱፻፸፭፣ ፲፱፻፸፱፣ ፲፱፻፹፫፣ ፲፱፻፹፯፣ ፲፱፻፺፩፣ ፲፱፻፺፭፣ ፲፱፻፺፱፣ ፳፻፫፣ ፳፻፯፣ ፳፻፲፩፣፳፻፲፭እና ፳፻፲፱ ዓመታተ ምሕረት ይቆጠራሉ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - በሰሌዳ ቁጥር ኢቲ-ኤቢ ኤክስ የተመዘገበው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዲ-ሲ ፫ (Douglas C-47-DL) አየር ዠበብ ከባሕር-ዳር ወደ ደብረ ማርቆስ ሲበር ከጮቄ ተራራ ላይ ተላትሞ ወደቀ። ከተሳፈሩትም ዘጠኝ ሰዎች መኻል አንድ መንገደኛ ብቻ ሲሞት ሌሎቹ ተርፈዋል።
- ፲፱፻፺፱ ዓ/ም - ሩሲያ በዓለም አቀፍ ረገድ ‘የፈንጂዎች አባት’ (Father of all bombs) ተብሎ የተሠየመውን ወደር-የለሽ ትልቅ ቦምብ በሙከራ አፈነዳች።
ልደት
ለማስተካከልዕለተ ሞት
ለማስተካከል- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - የሶቪዬት ኅብረት መሪ የነበሩት የዮሴፍ ስታሊን ተከታይ፣ ኒኪታ ክሩስቾቭ በዚህ ዕለት በ፸፯ ዓመት ዕድሜያቸው አረፉ።
- ፲፱፻፸፱ ዓ/ም - በአምሣዎቹና ስድሳዎቹ አሥርተ ዓመታት ‘ቦናንዛ’ በተባለው የትይዕንተ መስኮት (ቴሌቪዥን) ትርዒት ‘ቤን ካርትራይት’ የነበረው ካናዳዊው ተዋናይ፣ ሎርን ግሪን በተወለደ በ፸፪ ዓመቱ አረፈ።
- ፲፱፻፸፱ ዓ/ም - ፒተር ቶሽ፣ ጃማይካዊው የ’ሬጌ’ ሙዚቀኛ፣ በኪንግስተን ጃማይካ መኖሪያ ቤቱ ሊዘርፉት በገቡ ሌቦች እጅ ተገደለ።
ዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- (እንግሊዝኛ) <http://aviation-safety.net/database/record.php?id=19690311-0 Archived ማርች 21, 2016 at the Wayback Machine>. [Accessed 11 February 2011.]
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |