ጥቅምት ፲፩
(ከጥቅምት 11 የተዛወረ)
ጥቅምት ፲፩
ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፵፩ኛው እና የመፀው ፲፮ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፫፻፳፭ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ዮሐንስ ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፳፬ ዕለታት ይቀራሉ።
- ፲፭፻፲፫ ዓ.ም - የፖርቱጋል ተወላጅ ፈርዲናንድ ማጄላን በደቡብ አሜሪካ ደቡባዊ ጫፍ ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ወደ ሰላማዊ ውቅያኖስ መርከብ የሚያስተላልፍ በስሙም የሚጠራውን የማጄላን ስትሬይት (Magellan Straits) አገኘ።
- ፲፯፻፺፰ ዓ.ም. - በታዋቂው የብሪታንያ የባህር ኃይል አበጋዝ ሆሬሽዮ ኔልሰን መሪነት ከፈረንሳይና ከእስፓኛ ከተውጣጣ የባሕር ኃይል ጋር የትራፋልጋር ውጊያ (Battle of Trafalgar) እየተባለ በታሪክ በሚታወቀው ጦርነት የብሪታንያ ኃይል ድልን ተቀናጀ። ሆሬሽዮ ኔልሰንም በዚሁ ውጊያ ሞተ።
- ፲፰፻፵፯ ዓ.ም - የመጀመሪያዋ ሐጽናሚ[1] (Medical Nurse) በመባል ስሟ የሚታወቀው ፍሎሬንስ ናይቲንጌል ከ፴፰ ሐጽናሚያን ጋር ወደ ክራይሚያ ጦርነት ዘመቱ።
- ፲፰፻፸፩ ዓ.ም - ከጨሊዛ[2] (carbon) የተሠራ ክር በመጠቀም ቶማስ አልቫ ኤዲሰን የመጀመሪያውን የጾፓስ[3] (electric) መብራት ብልቃጥ ሞከረ። ይኼውም መብራት ከመቃጠሉ በፊት ለ ፲፫ ሰዐት ተኩል አበራ።
- ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - የሮማ ኦሊምፒክ የማራቶን ድል አድራጊው አበበ ቢቂላበቶክዮ ውድድር የራሱን የኦሊምፒክ ክብረ ወሰን በመስበር በ2 ሰዓት 12 ደቂቃ 11.2 ሰከንድ አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ድልን ተቀዳጀ። ከዚህ ድል ከሰላሳ ስድስት ቀናት በፊት ትርፍ አንጀቱን በቀዶ ሕክምና አስወግዶ ስለነበረ፣ ድሉን ለሁለተኛ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሳያገግም በአዲስ ክብረ ወሰን ማሸነፉ በማራቶን ውድድር እስካሁን ድረስ አቻ የለሽ ጀግና አድርጎ አስመስክሮለታል።
- ፲፱፻፹፩ዓ.ም - የቀድሞው የፊሊፒንስ ፕሬዚደንት ፈርዲናንድ ማርቆስና ሚስታቸው ኢሜልዳ ማርቆስ በማጭበርበር ወንጀል ኒው ዮርክ ተከሰሱ።
ልደት
ለማስተካከል- ፲፰፻፳፮ ዓ.ም. - ዳይናማይትን የፈጠረ፤ ፖካርሲ[4] (chemist) ፤ መሐንዲስ እና የጦር መሣሪያ ሠሪ የነበረው እንዲሁም የኖቤል ሽልማትን የመሠረተው የስዊድን ተወላጅ አልፍረድ በርንሃርድ ኖቤልበዚህ ዕለት ተወለደ።
- ፲፰፻፺፰ ዓ/ም - የጋናው የመጀመሪያ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የመጀመሪያው ፕሬዚደንት ዶክቶር ክዋሜ ንክሩማ በዚህ ዕለት ተወለዱ።
ዕለተ ሞት
ለማስተካከልዋቢ መጻሕፍትና ማስረጃ ምንጮች
ለማስተካከል- ^ መስፍን አረጋ (ዲባቶ)፣ ሰገላዊ አማርኛ፣ ፳፻ ዓ.ም
- ^ መስፍን አረጋ (ዲባቶ)]]፣ ሰገላዊ አማርኛ፣ ፳፻ ዓ.ም
- ^ መስፍን አረጋ (ዲባቶ)]]፣ ሰገላዊ አማርኛ፣ ፳፻ ዓ.ም
- ^ መስፍን አረጋ (ዲባቶ]]፣ ሰገላዊ አማርኛ፣ ፳፻ ዓ.ም
- (እንግሊዝኛ) http://www.ghanaweb.com/GhanaHomePage/people/person.php?ID=177 (accessed Feb. 16, 2012)
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |