ግመል
- ለፊደሉ፣ ገምልን ይዩ።
ግመል ሙሉ ጣት ሸሆኔ ካላቸው እንስሳ የሚመደብ ለማዳ የቤት እንስሳ ወገን ነው። በዋነኛነት ጀርባው ላይ ባለው በስብ የተሞላ አካል (ሻኛ) ይታወቃል። ይህ ሻኛ የአረቦች ግመል በሚባለው ዝርያ ላይ አንድ ብቻ ሲሆን፣ ሌላው ዝርያ በሰሜን ምስራቅ እስያ የሚገኘው ባክትሪያን ግመል ደግሞ ሁለት ነው። በአብዛኛው ደረቅ በረሀ ለመኖር የሚመቻቸው ሲሆን በብዛት በምዕራብ እስያ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ እስያ ይገኛሉ። የሠው ልጅ የሚያለምዳቸው ለወተት ምርት፣ ለስጋ፣ ለግመል ጽጉር ልብስ (በተለይ ከባክትሪያን ግመል) እንዲሁም አልፎ አልፎ ለመጓጓዣ ስለሚጠቅሙ ነው።
የግመል ወተት በብዙ አገራት ይገዛልና ይጠጣል። በአረቢያ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ሶማሊያ፣ ሞሪታኒያና አሜሪካ በሱቅ ይሸጣል። የግመል ወተት የሚያስገኙ ዋና አገራት ሶማሊያ፣ ኬንያ፣ ማሊ፣ ኢትዮጵያ፣ ኒጄር፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ እና ሱዳን ናቸው።
የግመል ሥጋ ደግሞ ለብዙ አገራት ምግብነት ከፍ ያለ ዋጋ አለው። በተለይ የግመል ሥጋ የሚበላው በኤርትራ፣ ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ፣ ጂቡቲ፣ ሱዳን፣ ግብጽ፣ ሊብያ፣ ሶርያ፣ አረቢያና ካዛክስታን ይበላል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |