ያዋን
ያዋን (ዕብራይስጥ፦ יָוָן) በኦሪት ዘፍጥረት 10 መሠረት የያፌት ልጅና ከኖህ 16 ልጅ ልጆች አንዱ ነው።
የተለመደው አስተያየት ፍላቭዩስ ዮሴፉስ እንደሚለው፣ ያዋን የግሪክ ሕዝብ አባት ሆነ።
«ያዋን» ማለት በዕብራይስጥ ደግሞ ለግሪክ አገርና ለግሪኮች ሁሉ ይጠቅማል። የጥንት ምሥራቅ ግሪኮች ወገን «ኢዮኔስ» (ቀድሞ «ያዎኔስ») ወይም ኢዮናውያን የተዛመደ ነው። የግሪክ ሕዝብ ይህን በሚመሳስሉ ስሞች በመካከለኛ ምስራቅና በሕንድ (ሳንስክሪት፦ «ያዋና») ይታወቅ ነበር። በጥንታዊ ግሪኮች ልማድ ደግሞ የኢዮናውያን አባት የአፖሎ ልጅ ኢዮን ይባላል።
ዘፍጥረት 10 ደግሞ የያዋን ልጆች ይዘረዝራል፦
- ኤሊሳ - ጥንታዊ የቆጵሮስ ኗሪ ወገን ስም አላሺያ መሆኑ ባብዛኛው ይታስባል። ነገር ግን የአይሁድ መጽሐፍ ሰፈር ሃ-ያሻር (1400 ዓ.ም. ግድም) የአላማኒ (የጥንቱ ጀርመን ነገድ) አባት ይለዋል፤ እንዲሁም የፖርቱጋል ካቶሊክ ቄስ አንቶኒዮ ቪዬራ (17ኛው ክፍለ ዘመን) የሉሲታኒያ (ጥንታዊ የፖርቱጋል ብሔር) አባት ይለዋል።
- ተርሴስ - እንዲህ መሳይ ስም የነበረው ከተማ ጠርሴስ በደቡብ አናቶሊያ (ዘመናዊ ቱርክ) ይገኛል። ደግሞ በደቡብ እስፓንያ «ታርቴሶስ» የተባለ ጥንታዊ ከተማ ስለ ነበር፣ ሳሙኤል ቦሻር (1638 ዓ.ም.) ከተርሴስ እንደ ተነሣ ጽፈዋል።
- ኪቲም - በተለመደው ይህ የቆጵሮስ ከተማ ኪቲዮን መንስኤ ነው። የአይሁድ መጽሐፍ ዮሲፖን (10ኛው ክፍለ ዘመን) እንዳለው፣ የኪቲም ወገን በጣልያ ሰፍሮ የሮማውያን ዘር ሆነ።
- ሮድኢ - እንደ ሮዶስ ደሴት ኗሪዎች አባት ይቆጠራል።
በትንቢተ ዳንኤል 8:21-22 እና 11:2 የያዋን ንጉሥ ሲጠቀስ ይህ ታላቁ እስክንድር ማለት እንደ ሆነ ብዙ ጊዜ ይተረጎማል።