የካ ሚካኤል
የካ ሚካኤል የአለት ውቅር ቤተክርስቲያን ሲሆን ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ በሚገኘው የየካ አምባ ላይ ይገኛል። ቤተክርስቲያኑ የላሊበላ ውቅር ቤተክርስቲያን አይነት ስልት የያዘ ነበር። ምንም እንኳ የህንጻው አወቃቀር ባልታወቀ ምክንያት ሳይጠናቀቅ የቀረ ቢሆንም ስራው ቢገባደድ ኑሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት የአለት ውቅር ቤተክርስቲያኖች በትልቅነቱ ሁለተኛ ይሆን እንደነበር ተመራማሪዎች ይዘግባሉ (ታላቁ የላሊበላ መድሃኒ አለም ነው)[1]።
| ||||
---|---|---|---|---|
የካ ሚካኤል | ||||
[[ስዕል:|250px]] | ||||
የካ ሚካኤል | ||||
አገር | ኢትዮጵያ | |||
ዓይነት | ||||
አካባቢ** | ||||
የቅርስነት ታሪክ | ||||
ቅርሱ የተሰራበት ዘመን | ||||
* የአለበት ቦታ ** የዩ.ኔ.ስ.ኮ. ክልል ክፍፍል |
ከትውፊት አንጻር፣ ቤተክርስቲያኑ የተሰራው በዓፄ አፅብሐትዕዛዝ እ.ኤ.አ በ380 ዓ.ም. ነው። ታሪክ አጥኝው ኤ.ኤፍ.ማቲው ግን ቤተክርስቲያኑ ከላሊበላ ዘመን በኋላና ከግራኝ መነሳት በፊት እንደተመሰረተ ያስረዳል[1]። የቤተክርስቲያኑ ስራ መቋረጥም አካባቢው በግራኝ በመወረሩ እንደሆነ ያስረዳል።
30% የሚሆነው የዋሻ ሚካኤል ህንጻ ሳይጠናቀቅ የቀረ ነው። ከዚያ በላይ ህንጻው የጣሪያና የግድግዳ መፍረስ አጋጥሞት በአሁኑ ዘመን ከሞላ ጎደል የመፈራረስ መልክ ይዞ ይገኛል። ለመፍረሱ ብዙ ምክንያት ይሰጣል፣ አንድ አንዶች በኢጣሊያ ወረራ ወቅት በቦምብ ተደብድቦ ነው ሲሉ ሌሎች ደግሞ በግራኝ ተቃጥሎ ነው ይላሉ። አንድ አንድ ተመራማሪዎች ግን ከራሱ ከቤተክርስቲያኑ ባገኙት መረጃ ተነስተው ህንጻውን ሲያንጹ የነበሩ ሰዎች ባደረጉት የሥነ ህንጻ ስህተት ጣሪያው እንደፈረሰ ያስረዳሉ።
በአሁኑ ወቅት፣ ምንም እንኳ ቤተክርስቲያኑ ከአዲስ አበባ ከተማ ትንሽ ወጣ ብሎ ያለ ቢሆንም የከተማው ነዋሪ ትኩረት ስለማይሰጠውና በቱሪስቶችም ዕውቅና ስሌለው በዛፍ ስርና በዝናብ የበለጠ ጉዳት እየደረሰበትና ቀስ በቀስ እየጠፋ ይገኛል።