አዳዲ ደብረ ምሕረት ቅድስት ማርያም ( አንፋር ደብረ ምሕረት ቅድስት ማርያም) ቤተ ክርስቲያን ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ሰባ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ፣ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት፣ በሌመን ወረዳ ውስጥ የምትገኝ እንደ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ከወጥ ድንጋይ ተፈልፍላ የተሠራች ጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን ናት። ቤተ ክርስቲያኒቱ በመቸ ዓመተ ምህረት እንደተሠራች እርግጠኛ መረጃ የለም። ሆኖም ግን በአጠቃላይ መልኩ በ፲፫ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደተመሰረተች ይታመናል። ይኸውም ከላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ሥራ ፍጻሜ ቀጥሎ መሆኑ ነው።

ከአለት የተፈለፈለ
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን
አዳዲ ማርያም(አንፋር ማርያም) [1]

[[ስዕል:|250px]]
የአዳዲ ወለል ማርያም አቅድ[1]
አገር ኢትዮጵያ
ሌላ ስም {{{ሌላ ስም}}}
ዓይነት
አካባቢ**
የቅርስነት ታሪክ
ቅርሱ የተሰራበት ዘመን  
አዳዲ ማርያም(አንፋር ማርያም) [1] is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
አዳዲ ማርያም(አንፋር ማርያም) [1]
ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ
* የአለበት ቦታ
** የዩ.ኔ.ስ.ኮ. ክልል ክፍፍል

ቤተ ክርስቲያኒቱ ከተመሰረተች ጀምሮ እስከ ፲፮ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ለአምልኮ ስታገለገለግል ቆይታ በኋላ በዚሁ ዘመን በተነሳው ግርግር ምክንያት ቤተ ክርስቲያኗን ለማትረፍ ሲባል በአፈር ተሞልታ በምድር ተቀበረች። ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ፲፰፻፹፯ ዓ/ም ከተቀበረችበት እስካስወጧት ድረስ ቤተ ክርስቲያኒቱ በተቀበረችበት ተረስታ ቆየች። በዚህ ምክንያት ቤተ ክርስቲያኒቱ ከውሃና እጽዋት ጉዳት በስተቀር ብዙ ጥፋት ሳይደርስባት አሁን ድረስ ትገኛለች። በ፲፱፻፺ ዓ/ም በስዊዘርላንድ የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ኮሚሽን አማካይነት አሥራ ስምንት ወራት የወሰደ እደሳ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ተካሂዶ በአሁኑ ወቅት ከ፳፭ እስከ ፴ ሺ ምዕመናን ፣ ፴፭ሺ ጎብኝዎች (ከኒህ ውስጥ ፯ሺ የውጭ ዜጎች) በየዓመቱ ታስተናግዳለች።

አዳዲ ደብረ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሥዕላት የላትም ነገር ግን እንደ ጥንቱ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አሠራር የተለያዩ ጌጦች ነበራት። ቤተ ክርስቲያኗ ፲፱ ሜትር ተኩል እርዝመት ሲኖራት ፲፮ ሜትር ወርድና ፮ ሜትር ቁመት አላት። ወደ ቤተ ክርስቲያኒቱ ለመግባት ሦስት አይነት ደረጃዎች አሉ፡- ሁለቱ ለወንዶችና ቀሳውስት ሲያገለግሉ አንዱ ደግሞ ለሴቶች ያገለግላል። ጣሪያዋ በሳር የተሸፈነ ስለሆነ ከሩቅ ለማየት ያዳግታል፣ ቤተ ክርስቲያኗ ከከባት አለት በመካከል በተሠራ መተላለፊያ የተለየች ሲሆን ከባቢው አለት ውስጥ ተፈልፍለው የተሰሩ ቀዳዶች ለመጸለያና ለመጾሚያ ያገለግላሉ። ዋናዋ ቤተ ክርስቲያን ሁለት ክፍል አላት፡ አንዱ ለቀሳውስት ሲሆን ሁለተኛው ድርሳኖችን ይይዛል። ምዕመናን እና ዘማሪዎች በነዚህ ክፍሎች ዙርያ ባለው በመተላለፊያው ይሰየማሉ።


[2]

ማጣቀሻ ለማስተካከል

  1. ^ Anray, Francis. Chronique archéologique, 1960-1964 In: Annales d'Ethiopie. Volume 6, année 1965. pp.48.
  2. ^ nfray, Francis. Chronique archéologique, 1960-1964 In: Annales d'Ethiopie. Volume 6, année 1965. pp.48.